Daniel Amdemichael/Yehonal/Destayie

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ ደስታዬ በጌታ ሙሉ ነው ከእንግዲህ ምንስ ያሻኛል ምድር ከሚታየው ሃብት ይልቅ የአምላኬ ፍቅር ማርኮኛል የምድር ዝና ከበሬታ ሃላፊ ነው ትቼዋለሁ የአምላኬ ክብር ባለበት የእኔስ ሃገር በሠማይ ነው ኦ ቃሉ እንደሚናገረው ሃሌሉያ

እኔስ በአደባባዮቹ መዋል ማደር ይሻለኛል የአምላኬ ክብር ሲገለጥ ውስጤን ልቤን ያረካኛል የኢየሱስ ፍቅር ብርቱ ነው ዘወትር አይለወጥም በቸርነቱ ይዞኛል ከቤቱ የትም አልሄድም

አዝ ደስታዬ በጌታ ሙሉ ነው ከእንግዲህ ምንስ ያሻኛል ምድር ከሚታየው ሃብት ይልቅ የአምላኬ ፍቅር ማርኮኛል የምድር ዝና ከበሬታ ሃላፊ ነው ትቼዋለሁ የአምላኬ ክብር ባለበት የእኔስ ሃገር በሠማይ ነው ኦ ቃሉ እንደሚናገረው ሃሌሉያ

ለእኔስ ማረፊያ ጌታ የዘለዓለም መኖሪያዬ ክብሩን አይቼ እጠግባለሁ ሞገስ ፈሷል በላዬ ከእርሱ ጋር መሆን እመርጣለሁ የእርሱ ክብር በሞላበት መኖሪያዬን አድርጐታል እግዚአብሔር በሚገኝበት።

አዝ ደስታዬ በጌታ ሙሉ ነው ከእንግዲህ ምንስ ያሻኛል ምድር ከሚታየው ሃብት ይልቅ የአምላኬ ፍቅር ማርኮኛል የምድር ዝና ከበሬታ ሃላፊ ነው ትቼዋለሁ የአምላኬ ክብር ባለበት የእኔስ ሃገር በሠማይ ነው ኦ ቃሉ እንደሚናገረው ሃሌሉያ

ጌታዬ በሚገኝበት ንጉሱ በሚገኝበት ሁሉን ቻይ በሚገኝበት