Daniel Amdemichael/Anbesa/Yenie Wedaj

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ የእኔ ጌታ /የእኔ/ ወዳጅ ኢየሱስ ነው ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም በጣም ተዋደናል አንለያይም (፪x)

ከልጅነት የተሸከመኝ እስከሽምግልና የሚመራኝ አሳዳጊ ይህ ወላጅ የሆነኝ ያለእርሱ ወገን ማነው ያለኝ

አዝ የእኔ ጌታ /የእኔ/ ወዳጅ ኢየሱስ ነው ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም በጣም ተዋደናል አንለያይም (፪x)

ቢከፋኝ ቢደላኝ እርሱ ነው ሁልጊዜ ከጐኔ ማገኘው ከእናት ከአባት በላይ ወዳጄ ኢየሱስ ነው ተቆርቋሪ ለእኔ

አዝ የእኔ ጌታ /የእኔ/ ወዳጅ ኢየሱስ ነው ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም በጣም ተዋደናል አንለያይም (፪x)

እግሬን ከጨለማ መልሷል በፍቅሩ ገመድ ውስጤን አስሯል ልዩ ነው ልዩ ነው ለእኔ በፍቅሩ ተማርካለች ነፍሴ

አዝ የእኔ ጌታ /የእኔ/ ወዳጅ ኢየሱስ ነው ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም በጣም ተዋደናል አንለያይም (፪x)

ሕያው ነው ምንም አያረጅም ዘመን ሲያልፍ እርሱ አይለወጥም ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ታማኝነቱ ለእኔ ብዙ ነው

አዝ የእኔ ጌታ/የእኔ ወዳጅ ኢየሱስ ነው ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም በጣም ተዋደናል አንለያይም (፪x)

በጣም ተዋደናል አንለያይም (፪x)