Daniel Amdemichael/Anbesa/Oh Temesgen

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል ርዕስ ኦ ተመስገን አልበም አንበሳ

አዝ ኦ ተመሥገን (፪x) ስላደረክልኝ ድንቅ ነገር ስላደረክልኝ መልካም ነገር ምስኪኑን ረዳኸኝ ከትቢያ አነሳኸኝ አልችልም እኔስ ልገልፀው ውለታህ በዛብኝ (፪x)

የምህረት ዓይኖችህ ይከታተሉኛል የበደሌን ብዛት ጌታ ፍቅርህ ሸፍኖታል ሀዘንም ሲያጠቃኝ ከጐኔ ቆመሃል መፅናናቴ ነህ ኢየሱስ አበርትተኸኛል (፪x)

አዝ ኦ ተመሥገን (፪x) ስላደረክልኝ ድንቅ ነገር ስላደረክልኝ መልካም ነገር ምስኪኑን ረዳኸኝ ከትቢያ አነሳኸኝ አልችልም እኔስ ልገልፀው ውለታህ በዛብኝ (፪x)

ጌታዬ ተባረክ ሁሉም በአንተ ሆነ አንድ ሁለት ብዬ የማወራው የለም ከእኔ የሆነ እውነት ነፍሴን ላፍስስ ሥምህን ልወድሰው የመዝሙሬ ዜማ ቅኔው ማደሪያህን ይሙላው (፪x)

አዝ ኦ ተመሥገን (፪x) ስላደረክልኝ ድንቅ ነገር ስላደረክልኝ መልካም ነገር ምስኪኑን ረዳኸኝ ከትቢያ አነሳኸኝ አልችልም እኔስ ልገልፀው ውለታህ በዛብኝ (፪x)

በሰው የተናቀ የተጣለውን ሰው መደነቂያ እንዲሆን ጌታ ለክብርህ አቆምከው ብርታት ትሆናለህ ሞገስ ትሆናለህ ኧረ እንዳንተ ማነው ጌታ/ኢየሱስ/ ሁሉን ትችላለህ (፪x)

አዝ ኦ ተመሥገን (፪x) ስላደረክልኝ ድንቅ ነገር ስላደረክልኝ መልካም ነገር ምስኪኑን ረዳኸኝ ከትቢያ አነሳኸኝ አልችልም እኔስ ልገልፀው ውለታህ በዛብኝ (፪x)

አስደናቂው ፍቅርህ ከሳበኝ ጀምሮ ያደረክልኝ ውለታ አያልቅም ተቆጥሮ ጌታ የአንተ ሥራ በምን ቋንቋ ልግለፅ ማለት የምችለው ይኸን ነው ኢየሱስ /ውድዬ/ ተባረክ (፪x)

አዝ ኦ ተመሥገን (፪x) ስላደረክልኝ ድንቅ ነገር ስላደረክልኝ መልካም ነገር ምስኪኑን ረዳኸኝ ከትቢያ አነሳኸኝ አልችልም እኔስ ልገልፀው ውለታህ በዛብኝ (፬x)