አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ (Antew Neh Gietayie) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 2.jpg


(2)

ጌታ ፡ አለ ፡ ከጐኔ
(Gieta Ale Kegonie)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 7:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

አንተው ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ መታመኛ
አንተው ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ መደገፊያ (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ትክክል ፡ ነው ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው
ማን ፡ ይቀራል ፡ እንባው ፡ ፈሶ ፡ ይታበሳል ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ
መታመኛው ፡ እግዚአብሔር ፡ ማረፊያውም ፡ ከጥላው ፡ ሥር
በኩፉ ፡ ቀናት ፡ ከጐኑ ፡ ሆኖለታል ፡ በዘመኑ

አዝ፦ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፪x)
ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፬x)

እንዳተ ፡ ያለ ፡ መልካም ፡ ለሰው ፡ የሚራራ
የተዋረደውን ፡ ደርሶ ፡ የሚያኮራ
አላገኘሁም ፡ እኔስ ፡ እስከ ፡ እድሜዬ ፡ ልክ
እወድሃለሁኝ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የኔ ፡ አምላክ

አዝ፦ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፪x)
ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፬x)

ቅዱስ ፡ ሥሙ ፡ እንዲጠራ ፡ ትልቅ ፡ ታሪክ ፡ በእኔ ፡ ሰራ
ጠላቶቼን ፡ አሳፍሮ ፡ ታየ ፡ ጌታ ፡ በኔ ፡ ከብሮ
አልቀረሁም ፡ እንደወደቅኩ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ መቼ ፡ አፈርኩ
አጥር ፡ ቅጥሩን ፡ እየዘለልኩ ፡ እኖራለሁ ፡ እያመለኩ

አዝ፦ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፪x)
ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፬x)

አቅም ፡ ጉልበት ፡ ስለሌለው ፡ የት ፡ ይደርሳል ፡ የተባለው
ዛሬ ፡ ታዲያ ፡ ለዚህ ፡ ክብር ፡ ለዚህ ፡ ሹመት ፡ ማን ፡ አበቃው
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ተስፋ ፡ መድረሻ ፡ አለው ፡ እንዳይጠፋ
ያግዘዋል ፡ የታመነው ፡ ያኮራዋል ፡ የሚያመልከው

አዝ፦ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፪x)
ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፬x)

ቅዱስ ፡ ሥሙ ፡ እንዲጠራ ፡ ትልቅ ፡ ታሪክ ፡ በእኔ ፡ ሰራ
ጠላቶቼን ፡ አሳፍሮ ፡ ታየ ፡ ጌታ ፡ በእኔ ፡ ከብሮ
አልቀረሁም ፡ እንደወደቅኩ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ መቼ ፡ አፈርኩ
አጥር ፡ ቅጥሩን ፡ እየዘለልኩ ፡ እኖራለሁ ፡ እያመለኩ

አዝ፦ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፪x)
ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፬x)

እንዳንተ ፡ ያለ ፡ መልካም ፡ ለሰው ፡ የሚራራ
የተዋረደውን ፡ ደርሶ ፡ የሚያኮራ
አላገኘሁም ፡ እኔስ ፡ እስከ ፡ እድሜዬ ፡ ልክ
እወድሃለሁኝ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ አምላክ

አዝ፦ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፪x)
ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፬x)