የከበረ ፡ ቤቴ ፡ በላይ (Yekebere Biete Belay)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የከበረ ፡ ቤቴ ፡ በላይ
ማን ፡ ይተርካል ፡ መድመቋን?
የተመረጡት ፡ እንደ ፡ ፀሐይ
ይደምቃሉ ፡ በአምላክ ፡ ብርሃን ።
በሰማይ ፣ በሰማይ
የከበረ ፡ ቤቴ ፡ በላይ
በሰማይ ፣ በሰማይ
ኦ! ብፁዕ ፡ ሰላም ፡ በሰማይ ።

በእንዴት ፡ ያለ ፡ ግሩም ፡ ፍስሐ
ጉዟቸውን ፡ የጨረሷት
የማይተረክ ፡ ሰላምና ፡ ደስታ
ያገኛሉ ፡ በፍቅሩ ፡ ብዛት ።
በሰማይ ፣ በሰማይ
የከበረ ፡ ቤቴ ፡ በላይ
በሰማይ ፣ በሰማይ
ኦ! ብፁዕ ፡ ሰላም ፡ በሰማይ ።

በዚያ ፡ መድኃኒቴ ፡ ነው
ቤተ ፡ ዘመዴም ፡ ሁሉ ፡ በአንድ
የዚህ ፡ ምድርን ፡ ሃዘን ፡ ልርሳው
ደስ ፡ ይበለኝ ፡ ከብፁዓን ፡ ዘንድ ።
በሰማይ ፣ በሰማይ
የከበረ ፡ ቤቴ ፡ በላይ
በሰማይ ፣ በሰማይ
ኦ! ብፁዕ ፡ ሰላም ፡ በሰማይ ።

በቶሎም ፡ ወዲያ ፡ ልግባ
የእንግድነቴ ፡ ዘመን ፡ ይለፍ
በዙፋኑም ፡ አንጻር ፡ በዕልልታ
ከወዳጆቼ ፡ ጋራ ፡ ልረፍ ።
በሰማይ ፣ በሰማይ
የከበረ ፡ ቤቴ ፡ በላይ
በሰማይ ፣ በሰማይ
ኦ! ብፁዕ ፡ ሰላም ፡ በሰማይ ።