የአባትህ ፡ ዕቅፍ ፡ ተከፍቷል (Yeabatih Eqif Tekeftoal)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የአባትህ ፡ ዕቅፍ ፡ ተከፍቷል
ልጁን ፡ ሊቀበልህ
በስምህም ፡ ይጠራሃል
በፍቅሩም ፡ ፈለገህ
እጁንም ፡ ዘርግቶልሃል
በታላቅ ፡ ምሕረት
ለአንተም ፡ ተዘጋጅቷል
ሥፍራ ፡ በሠርጉ ፡ ቤት

በዚህ ፡ በዓለም ፡ በረሃ
ሰላም ፡ የማታገኝ
ከሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ጥሩ ፡ ውሃ
እንዴት ፡ የማትመኝ
በሌላ ፡ ምንጭ ፡ የልብህ ፡ ጥም
ሊጠፋ ፡ አይችልም
መድኃኒት ፡ ያለ ፡ ኢየሱስ ፡ ስም
አልተገኘልንም

ርስትህን ፡ ሁሉ ፡ በትነህ
መሞት ፡ ያስፈራሃል
በቤትህ ፡ ግን ፡ ቸር ፡ አባትህ
ልጁን ፡ ይጠብቃል
የሠርግ ፡ ልብስና ፡ ቀለበት
አሁን ፡ ይቆይሃል
በከንቱ ፡ ሁሉን ፡ ለመስጠት
አባትህ ፡ ወዷል

የጠፋ ፡ ልጅ ፡ ወዳባቱ
ቢሄድ ፡ በንስሐ
በማይመረመር ፡ ምሕረቱ
ይወርሳል ፡ ፍስሐ
በቤቱም ፡ ሁሉ ፡ ግሩም ፡ በዓል
ዕልልታም ፡ መዝሙርም
በዚያ ፡ ቀን ፡ ይደረጋል
ደስታውም ፡ አይተረክም