የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንኸው (YeEgziabher Beg Yehonkhew)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንኸው
ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ያበስኸው
ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ እስኪ ፡ ና!
የማዋይህ ፡ አለኝ ፡ ና!

ሳይሳሱ ፡ ከአገር ፡ አውጥተው ፡ ውርደት ፡ አለበሱህ
ስለፈወስክ ፡ አቁስለው ፡ በፍቅርህ ፡ የጠሉህ
የድሃ ፡ አዛኝ ፡ የሆንኸው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
ይገባህ ፡ ነበር ፡ ወይ? ለእኔ ፡ አፈር ፡ ልትለብስ?

የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንኸው
ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ያበስኸው
ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ እስኪ ፡ ና!
የማዋይህ ፡ አለኝ ፡ ና!

አንተ ፡ ፍቅር ፡ ነህና ፡ ልትጠላኝ ፡ አቃተህ
ነፍሴን ፡ ከእሣት ፡ አወጣህ ፡ እራስህን ፡ ጐድተህ
የእኔ ፡ የሆነ ፡ ምን ፡ አለኝ? እራሴም ፡ የአንተው ፡ ነኝ
ስለዚህ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ! ደጋግመህ ፡ ለውጠኝ

የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንኸው
ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ያበስኸው
ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ እስኪ ፡ ና!
የማዋይህ ፡ አለኝ ፡ ና!

ኑሮዬና ፡ ተግባሬ ፡ ለእኔ ፡ ባይጥመኝም
ጠላት ፡ እግሬን ፡ እየወጋ ፡ ቢያደናቅፈኝም
አንድ ፡ ጊዜ ፡ ቆርጬ ፡ ተከትዬሃለሁ
ድካም ፡ እንኳ ፡ ቢያጠቃኝ ፡ እከተልሃለሁ

የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ የሆንኸው
ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ያበስኸው
ጓዴ ፡ ኢየሱስ ፡ እስኪ ፡ ና!
የማዋይህ ፡ አለኝ ፡ ና!