የአምላካችን ፡ ታናሽ ፡ ጭፍራ (YeAmlakachin Tanash Chifra)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የአምላካችን ፡ ታናሽ ፡ ጭፍራ
ቤቱ ፡ ነው ፡ በፅኑ ፡ ሥፍራ
ኮከብ ፡ በሰማዩ ፡ ጠፈር
እንደ ፡ ልጆቹም ፡ አይደፍር

ልጆቹ ፡ ባምላክ ፡ ተራራ
ይኖራሉ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ
እርሱም ፡ ልጆቹን ፡ ይጦራል
ሠርክ ፡ ሲጠብቅም ፡ ይኖራል

ደስታ ፡ ቢሆን ፡ ወይስ ፡ ጭንቅም
ልጁን ፡ ከእርሱ ፡ እጅ ፡ አይነጥቅም
ያ ፡ ወዳጅ ፡ በፅኑ ፡ እጁ
ጋሻ ፡ መክቷል ፡ ለልጁ

የራስ ፡ ጠጉራችን ፡ ሁሉ
ባምላክ ፡ ዓይን ፡ ይቆጠራሉ
አምላክም ፡ ይመግበናል
በእርሱም ፡ ፍቅር ፡ ደስ ፡ ይለናል

አንዳችን ፡ ቢሰጥ ፡ ቢነሣም
አባትነቱን ፡ አይረሳም
ሃሣቡም ፡ ለጥቅማችን
ነው ፡ በመላ ፡ ዘመናችን

ደስ ፡ ይበልህ ፡ ታናሽ ፡ መንጋ
አምላክህን ፡ አትዘንጋ
በእርሱ ፡ ኃይል ፡ ጠላቶች ፡ ሁሉ
ቢነሡብህ ፡ ይጠፋሉ