ያ ፡ ታላቅ ፡ ሐኪም ፡ መጥቷል (Ya Talaq Hakim Mettitoal)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ያ ፡ ታላቅ ፡ ሐኪም ፡ መጥቷል
መድኃኒታችን ፡ ኢየሱስ
ለዓለምም ፡ ተሰጥቷል
መዳን ፡ በጌታ ፡ ኢየሱስ
ሥሙ ፡ ይላቅ ፡ ለትጉሃን
ይዘመርም ፡ በሰው ፡ ልሣን
ይደነቅ ፡ ለምዕመናን
ያ ፡ ድንቅ ፡ ሥም ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ

የአምላክ ፡ በግ ፡ ሆኖልናል
መድኃኒታችን ፡ ኢየሱስ
በመስቀልም ፡ ሞቶልናል
ያ ፡ ንጹሕ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ሥሙ ፡ ይላቅ ፡ ለትጉሃን
ይዘመርም ፡ በሰው ፡ ልሣን
ይደነቅ ፡ ለምዕመናን
ያ ፡ ድንቅ ፡ ሥም ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ

ዕዳችንን ፡ ይሠርያል
መድኃኒታችን ፡ ኢየሱስ
ወደ ፡ ሰማይ ፡ ይመራናል
ያ ፡ ቸር ፡ እረኛ ፡ ኢየሱስ
ሥሙ ፡ ይላቅ ፡ ለትጉሃን
ይዘመርም ፡ በሰው ፡ ልሣን
ይደነቅ ፡ ለምዕመናን
ያ ፡ ድንቅ ፡ ሥም ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ