ወዴት ፡ አመልጣለሁ ፡ ከአምላኬ ፡ ፊት (Wodet Amelttalehu KeAmlakie Fit)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ወዴት ፡ አመልጣለሁ ፡ ከአምላኬ ፡ ፊት?
ሰው ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ የሚሰወር
የሚያስፈራራ ፡ የፍርድ ፡ ቀን ፡ ሲብት
እንዴትም ፡ ልቆም ፡ ያለ ፡ ነውር
ለእኔ ፡ ኃጢአተኛ ፡ ራራልኝ

ሽቅብ ፡ ብመለከት ፡ ፍርሃት ፡ ይዞኛል
ከዓርያም ፡ ይመጣል ፡ ዳኛዬ!
ቁልቁል ፡ ብመለከት ፡ ያስፍረኛል
በምድር ፡ ተጻፈ ፡ ኃጢአቴ
ለእኔ ፡ ኃጢአተኛ ፡ ራራልኝ

ኦ! ኢየሱስ ፡ በመስቀል ፡ ስለ ፡ ፈሰሰ
ስለ ፡ ደምህ ፡ ይቅር ፡ በልልኝ
ስትመጣ ፡ ለፍርድ ፡ ኢየሱስ ፡ በርኅራኄ
ነጻ ፡ አውጥተህ ፡ ስመርልኝ
ለእኔ ፡ ኃጢአተኛ ፡ ራራልኝ