ጠውልጐ ፡ ሲቀር ፡ የዓለም ፡ ተስፋ (Tewulgo Siqer Yealem Tesfa)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ጠውልጐ ፡ እንደ ፡ አበባ
ሲቀር ፡ የዓለም ፡ ተስፋ
ውኃ ፡ ፈልቆ ፡ በበረሃ ፡ ለተጸማ
ነፍሱን ፡ የሚያረካ

ክርስቶስ ፡ ፍቅሩን ፡ እያሳየን
የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ሆነልን
በደሙ ፡ የሚያድነን ፡ ለነፍሣችን
ሃብቱን ፡ አቀረበልን

በዓለም ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ብቻ
ከጭንቀት ፡ የሚረዳ
ሊሰጥ ፡ ለኃጢአን ፡ ይቅርታ
ምሉዕ ፡ ፀጋ
ኑዛዜ ፡ ለሚገባ

ከኢየሱስ ፡ ነው ፡ ብርሃን ፡ ዕውነት
ሆነልን ፡ መንገድ ፡ ሕይወት
የፈለገው ፡ ያገኘዋል
ይሰጠዋል
ለለመነው ፡ በዕምነት

በመላ ፡ ዕድሚያችን ፡ ቀን
እጆቹን ፡ ዘረጋልን
ገና ፡ እኛን ፡ ይታገሣል
ይጦረናል
ዕምነትን ፡ አጸናልን

በጐ ፡ እረኛ ፡ ሆኗል
የጐደለውን ፡ ይሞላል
በወንጌል ፡ በቅዱስ ፡ እራት
ሰጠን ፡ ብጽአት
ርኅሩኅ ፡ ሆኖ ፡ ይኖራል

ከኩነኔ ፡ ሊያድነን
ስንት ፡ ውለታ ፡ ዋለልን
ድል ፡ ይሰጣል ፡ በጦርነት
በቸርነት
ሆነልን ፡ ጤና ፡ ሕይወት

እንደ ፡ አባት ፡ አሳድረን
ፀጋህን ፡ አቅርብልን
ሰላምን ፡ ስጥ ፡ ለችጉር ፡ ነፍስ
ለእኛ ፡ ለግሥ
ይህ ፡ ጉዞ ፡ እስኪጨረስ

በሚደርስብን ፡ መከራ
ሆንህልን ፡ ረድዔት ፡ ተስፋ
በጭንቅ ፡ በሞት ፡ አሳልፈህ
በመንግሥትህ
ብጽዕናን ፡ ትሰጣለህ