ተራመድ ፡ በርታ ፡ ጉዞህንም ፡ ቀጥል (Teramed Berta Guzohenem Qettil)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ቀጥል
ሕይወትህንም ፡ አድን

የመከራ ፡ ጉም ፡ በላይህ ፡ ቢያንዣብብ
አለና ፡ ኢየሱስ ፡ ፍጹም ፡ አታስብ
ቢመስልህ ፡ ጉዞህ ፡ ፍፁም ፡ ተራራ
መጋቢ ፡ አለህ ፡ ፍጹም ፡ አትፍራ

አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ቀጥል
ሕይወትህንም ፡ አድን

በኃጢአት ፡ ቁስል ፡ ብትማቅቅም
በሥሜ ፡ ካመንክ ፡ ፍፁም ፡ አትወድቅም
ስለሚመለስ ፡ ጌታ ፡ ከሰማይ
መብራትህ ፡ ይብራ ፡ ለዓለምም ፡ ይታይ

አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ቀጥል
ሕይወትህንም ፡ አድን

አትሞኝ ፡ ከቶ ፡ በዓለም ፡ ደስታ
ስለማታገኝ ፡ የሕይወት ፡ ፋታ
መቅረዝህ ፡ ይብራ ፡ ቁም ፡ ተዘጋጅ
ጌታ ፡ ሲመለስ ፡ ትነጠቃለህ

አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ቀጥል
ሕይወትህንም ፡ አድን

ቋሚ ፡ ጓደኛ ፡ ስላለህ ፡ ኢየሱስ
በዕምነት ፡ ተጋደል ፡ በተስፋ ፡ ገስግስ
ዓለምን ፡ አትይ ፡ ማብለጭለጯንም
ተስፋ ፡ በመቁረጥ ፡ አታድንህም

አዝ፦ ተራመድ ፡ በርታ ፡ በርታ
ጉዞህንም ፡ ቀጥል
ሕይወትህንም ፡ አድን