ተነሥቼ ፡ ወዳባቴ ፡ ልሄድ ፡ ነኝ (Tenesiche Wodabatie Lihed Negne)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ተነሥቼ ፡ ወዳባቴ ፡ ልሄድ ፡ ነኝ
በቀና ፡ መንፈሥ ፡ ላድርግ ፡ ኑዛዜን
አምላኬ ፡ ሆይ! ምሕረትህን ፡ አሳየኝ
በፀጋ ፡ ደምስስልኝ ፡ ኃጢአቴን

እንዲህ ፡ ብዬ ፡ አባቴ ፡ ሆይ! ተወልኝ
በአንተና ፡ በሰማይም ፡ በደልሁ
ሰላም ፡ ስጠኝ ፡ ደስታህን ፡ አውርድልኝ
ተቀበለኝ ፡ ስል ፡ እጮሃለሁ

ይሰማኛል ፡ ኃጢአቴ ፡ እንደ ፡ በዛ
የአምላክ ፡ ምሕረት ፡ ገና ፡ ይበልጣል
ጥፉ ፡ ልጁ ፡ ልመለስ ፡ ሲል ፡ ቢነሣ
ቸር ፡ አባቱ ፡ አቅፎ ፡ ይቀበላል

ተነሥቼ ፡ ወዳባቴ ፡ ልመለስ
ልማጠን ፡ ነኝ ፡ በአባትነቱ
ጉባዔ ፡ ብጹዓን ፡ ለአምላክ ፡ ሊወድስ
ሲገባ ፡ ጥፉ ፡ ልጅ ፡ በማኅበሩ