ስለ ፡ ሕይወት ፡ ዋና ፡ ጥቅም (Sile Hiwot Wana Tiqim)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ስለ ፡ ሕይወት ፡ ዋና ፡ ጥቅም
አምላኬ ፡ አስተምረኝ
በዓለም ፡ ያለ ፡ ቢያስገርም
ክቡድ ፡ ቀንበር ፡ ሆነብኝ
በፈተና ፡ ወጥመድ ፡ ያጠላልፈኛል
ሥቃይና ፡ ሁከትን ፡ ዘወትር ፡ ያመጣል
ሁሉን ፡ የሚተካ ፡ ያ ፡ አንዱን ፡ ባገኝ
በሚደርስብኝ ፡ ዕጉሥ ፡ ብፁዕ ፡ ነኝ

ልታገኘው ፡ ብትታገል
አተሻ ፡ በከንቱነት
ከዓለም ፡ ምኞት ፡ ተጠቃለል
ከፍ ፡ በል ፣ ዝቅ ፡ ካለ ፡ ፍጥረት
በአምላክ ፡ ስትጠጋ ፡ ስትታመን ፡ ፍቅሩን
በኢየሱስ ፡ ይሰጥሃል ፡ ነዋሪ ፡ ሃብቱን
ያን ፡ ዕድል ፡ ያገኘ ፡ በጉድለቱ ፡ እንኳ
ዘወትር ፡ ይኖራል ፡ በትርፍ ፡ በደስታ

ይህን ፡ ዕድል ፡ ለማግኘት
ማርያም ፡ እየናፈቀች
ለመስማት ፡ የጌታን ፡ ትምህርት
ዝቅ ፡ ብላ ፡ ተቀመጠች
በተነገረላት ፡ ሰማያዊ ፡ ዕውነት
ብርሃኑ ፡ ወጣላት ፣ ፍቅሩ ፡ አሞቃት
ያ ፡ መልካሙ ፡ ዕድል ፡ ሳይወሰድባት
ለዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ተጠበቀላት

ቸሩ ፡ ኢየሱስ ፣ ሕዙን ፡ ልቤ
ወደ ፡ አንተ ፡ ይናፍቃል
በፍቅር ፡ ተባበር ፡ ከእኔ ፡
አድርገኝ ፡ የአንተ ፡ አካል ።
ሌሎች ፡ ከአንተ ፡ ርቀው ፡ ቢጠፉብህ ፡ እንኳ
ዘወትር ፡ ልኖርልህ ፡ ፍቅሬን ፡ አጽና
በቃልህ ፡ ይገኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ሕይወት
በጸጸት ፡ በጭንቀት ፡ ዘወትር ፡ ረድዔት ።

እንዲህ ፡ ያለ ፡ ሃብት ፡ ከሰጠህ
አሁን ፡ ምን ፡ ያጣብኛል
ደምህን ፡ ለመሥዋዕት ፡ ይዘህ
ወደ ፡ መቅደስ ፡ ገብተሃል
ከሞት ፡ ኃይል ፡ አዳንህ ፣ ዋጀህ ፡ ከባርነት
የልጅነት ፡ መንፈስ ፡ ላክህ ፡ በቸርነት
ዓርነት ፡ ካገኘሁ ፡ በአንተ ፡ የውሃት
ካሁን ፡ ልገዛልህ ፡ በቅዱስ ፡ ቅናት ።

አሁን ፡ ሰላም ፡ ደስታ ፡ አለኝ
ተስፋዬ ፡ በኢየሱስ ፡ ነው
በዓለም ፡ አቃንቶ ፡ ሊመራኝ
መንፈሴን ፡ ሊቀድሰው
ልኖር ፡ በቸርነት ፡ በፅድቅ ፡ በበጐነት
አርቅ ፡ ግብዝና ፣ አግባልኝ ፡ ቅንነት ።
በሕይወት ፡ በሞትም ፡ ሁንልኝ ፡ ተገን
ስብሃት ፡ ለአምላክ ፣ ለዘለዓለም ፡ አሜን ።