ስማልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ፀሎቴን (Semalegn Eyesus Tselotien)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ስማልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ፀሎቴን
አድርግ ፡ መቅደስህን ፡ በውስጤ
አግባ ፡ ሰላምን ፡ በልቤ
ኦ ! ኢየሱስ ፡ አትራቅ ፡ ከእኔ

የዋህ ፡ አባት ፡ ሆነህ ፡ ምራኝ
ሲጨልም ፡ ብርሃን ፡ ሁንልኝ
አንተን ፡ በሁሉ ፡ ደስ ፡ ላሰኝ
የመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ኃይል ፡ ስጠኝ

ልጁን ፡ ለላከ ፡ ለሃጥአን
ላደረገነ ፡ ብፁዓን
ቁጭ ፡ ላለ ፡ በሰማይ ፡ ዙፋን
ይሁን ፡ ግርማ ፡ ክብረት ፡ ሥልጣን