ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር (Qdus Qdus Qdus Egziabher)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር
ስብሐት ፡ ላንት ፡ በሰማይ ፡ ለምትኖር
ይገባናል ፡ ምሥጋናህን ፡ ልንዘምር
በልባችን ፡ ቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ ይደር

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር
ነዋሪ ፡ አምላክ ፡ በሰማይ ፡ በምድር
የምታቀልል ፡ የኃጢአትን ፡ ቀንበር
በምሕረትህ ፡ ስጠን ፡ ሰላም ፡ ፍቅር

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር
መሐሪ ፡ አምላክ ፡ በደልን ፡ የሚምር
ስንለምንህ ፡ በዔድን ፡ ገነት ፡ ልንኖር
አካፍለነ ፡ ከብጹዓን ፡ ማህበር