ቃል ፡ አለኝ ፡ የሚፈፀም (Qal Alegn Yemifetsem)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ቃል ፡ አለኝ ፡ የሚፈፀም ፡ አምላኬ ፡ የነገረኝ (፫x)
ሕልም ፡ አለኝ ፡ የሚፈታ ፡ ጌታዬ ፡ ያሳየኝ (፫x)

አዝ፦ በጅምር ፡ አይቀርም ፡ የኔ ፡ ነገር
ሳይጨርስ ፡ አያርፍም ፡ እግዚአብሔርም (፪x)

እገሰግሳለሁ ፡ ወዳየልኝ ፡ ክብር
ጠላት ፡ አይኑ ፡ እያየ ፡ ጆሮው ፡ እየሰማ (፪x)
ዮርዳኖስ ፡ ቢሞላ ፡ አይቀርም ፡ መሻገር
ጠላት ፡ አይኑ ፡ እያየ ፡ ጆሮው ፡ እየሰማ (፪x)
ዘልቄ ፡ እሄዳለሁ ፡ በምድሪቱ ፡ ስፋት
ጠላት ፡ አይኑ ፡ እያየ ፡ ጆሮው ፡ እየሰማ (፪x)

አዝ፦ በጅምር ፡ አይቀርም ፡ የኔ ፡ ነገር
ሳይጨርስ ፡ አያርፍም ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ይጨምራል ፡ ገና ፡ የቅባቱ ፡ ጉልበት
ጠላት ፡ አይኑ ፡ እያየ ፡ ጆሮው ፡ እየሰማ
አልቆምም ፡ እሄዳለሁ ፡ ጌታ ፡ ብሏልና
ጠላት ፡ አይኑ ፡ እያየ ፡ ጆሮው ፡ እየሰማ
አይሆንም ፡ አልልም ፡ ሆኖ ፡ ስለማየው
ጠላት ፡ አይኑ ፡ እያየ ፡ ጆሮው ፡ እየሰማ

አዝ፦ በጅምር ፡ አይቀርም ፡ የኔ ፡ ነገር
ሳይጨርስ ፡ አያርፍም ፡ እግዚአብሔር (፪x)

አምላኬ ፡ ሲጠራን ፡ ከዚያ ፡ መንደር ፡ ለትልቅ ፡ ቁም ፡ ነገር (፫x)
ኢየሱስ ፡ ሲጠራን ፡ ከዚያ ፡ ስፍራ ፡ ለትልቅ ፡ ቁም ፡ ነገር (፫x)

በምአልፈው ፡ በዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር
ጨከን ፡ በል ፡ ልቤ ፡ አትሸበር (፪x)

ለምን ፡ ተበሳጨ ፡ ያ ፡ ጠላቴ ፡ አይቶ ፡ መቀባቴን
ለምን ፡ ተበሳጨ ፡ ያ ፡ ጠላቴ ፡ አይቶ ፡ መነሳቴን

ስለምን ፡ ተመነው ፡ ጠላት ፡ ሞተን ፡ አይቶ ፡ መቀባቴን
ስለምን ፡ ተመነው ፡ ጠላት ፡ ሞተን ፡ አይቶ ፡ መነሳቴን

ከዚም ፡ የበለጠ ፡ ገና ፡ አለኝ
አምላኬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያሰበልኝ