ኦ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ለእኔ ፡ ና (Oh Menfes Qdus Leine Na)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኦ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ለእኔ ፡ ና
በልቤም ፡ ውስጥ ፡ ብርሃን ፡ አብራ
ከእኔም ፡ ጋር ፡ ተባበር
ዕውነትህን ፡ አስተምረኝ
የሕይወትም ፡ ውኃ ፡ ስጠኝ
ሥራህንም ፡ አዳብር

በዕውነት ፡ መንገድህ ፡ ምራኝ
ወደ ፡ አንተም ፡ እንድቀርብ ፡ ጥራኝ
በቃልህም ፡ እዘዘኝ
ከክፉውም ፡ ተለይቼ
ከኃጢአትም ፡ ጠርቼ
ልከተልህ ፡ አግዘኝ

አምላክ ፡ በመላ ፡ ሕይወቴ
በኢየሱስ ፡ በመድኃኒቴ
በዕውነት ፡ ለመታመን
የፀጋህን ፡ ረድዔት ፡ ስጠኝ
ለቅድስናም ፡ ኃይል ፡ ሁነኝ
አንተን ፡ ብቻ ፡ ልማጠን

ሰይጣን ፡ እንዳያሸንፈኝ
ዓለምም ፡ እንዳይደልለኝ
ከቶ ፡ አትራቅብኝ
ብፅዕናህንም ፡ እንድወርስ
እንዳለኝ ፡ የልጅነት ፡ ቅርስ
በልቤ ፡ መስክርልኝ

ስንፍናዬ ፡ ይሰማኛል
መለመንም ፡ ይሣነኛል
አንተ ፡ ግን ፡ ጸልይልኝ
ኦ! ርኅሩኅ ፡ መንፈስ ፡ በእኔ ፡ ኑር
የደከመውንም ፡ ልቤን ፡ ጡር
ከዓብም ፡ ለምንልኝ

በዕውቀትህ ፡ በፀጋህም
ፍሬ ፡ ለማፍራት ፡ ለማደግም
ዘወትር ፡ አነሣሣኝ
በሰጠኸኝ ፡ ቅዱስ ፡ መክሊት
ዘለዓለም ፡ የማያልቅ ፡ ጥሪት
እንዳገኝ ፡ አበርታታኝ

የደስታ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ! እርዳኝ
በጭንቀቴም ፡ ሁሉ ፡ አጽናኝ
በሞትም ፡ ድምጽ ፡ ስጠራ
እንደ ፡ ምዕመን ፡ እንድሞት
አጠንክረኝ ፡ በሃይማኖት
ነፍሴን ፡ ለአንተ ፡ አደራ