ኦ ፡ ቅዱስ ፡ መንፈስ ፡ የዕውነት ፡ መንፈስ (Oh! Qidus Menfes YeEwunet Menfes)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኦ! ቅዱስ ፡ መንፈስ
የዕውነት ፡ መንፈስ
መጥተህ ፡ ምራነ
አ በ ር ታ ነ
ኃይል ፡ ሲጐድልብን
ዕምነት ፡ ጨምርልን
በየዕለት ፡ ወደ ፡ ብፅዕና ፡ ሳበን
ጥበብ ፡ አቤቱ ፡ ስጠን ፡ ከዓርያም

ኦ! ቅዱስ ፡ መንፈስ
የሥልጣን ፡ መንፈስ
ነፍስን ፡ አሙቅልን
በየልባችን
ፍቅርን ፡ አስርጽብን
እንደ ፡ ፍሬ ፡ ሊወጣ
የውሃት ፡ ትዕግሥት ፡ ሰማያዊ ፡ ደስታ
ጽድቅን ፡ አቤቱ ፡ ስጠን ፡ ከዓርያም

ኦ! ቅዱስ ፡ መንፈስ
የደስታ ፡ መንፈስ
ደስታን ፡ አውርድልን
በመከራችን
አትግለልብን
ሲመሽብን ፡ ዕለት
ብርሃን ፡ ሁነኝ ፡ ሰላም ፡ በልብ ፡ አግባበት
አምላክ ፡ ብፅዕናን ፡ ስጠን ፡ ከዓርያም