ኑ ፡ እናንት ፡ ሰዎች (Nu Enant Sewoch)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኑ ፡ እናንት ፡ ሰዎች
ጌታን ፡ እናመስግን
አብራችሁም ፡ ልጆች
አመስግኑ ፡ ፍቅሩን
አክብሩ ፡ ፀጋውን

ሰማይና ፡ ምድር
በግርማ ፡ ሲመላ
የሰማይ ፡ ክብር
ትቶ ፡ በትሕትና
ስለእኛ ፡ ተገዛ

ያን ፡ ደዌያችን
እርሱ ፡ ተሸከመ
ኃጢአትን ፡ ሞትን
ለእኛ ፡ አሸነፈ
ሰላምን ፡ ሰጠነ

እኛን ፡ ሊበጀን
ንጹሑ ፡ ቆሰለ
ለርሱ ፡ ሊዋጀን
እጅግ ፡ ተጋደለ
በመስቀሉ ፡ ሞተ

ሊያዘጋጀን
ሙሽራው ፡ ልንሆን
ሞገስ ፡ ሊሰጠን
በሥሙ ፡ ስናምን
ጽድቁን ፡ ተላብሰን

በቃል ፡ በሥራ
ኢየሱስን ፡ ለማክበር
በሞቀ ፡ ደስታ
ስለ ፡ አምላክ ፡ ፍቅር
በመዝሙር ፡ እናክብር