ነጋ ፡ ሌሊቱ (Nega Lielitu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝነጋ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ (፪x)
በሰላም ፡ አደርኩኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ
እንደመሸ ፡ አልቀረም ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ
በሰላም ፡ አደርኩኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ
አንበሶች ፡ አልበሉኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ

የታመንኩት ፡ ጌታ ፡ ያድነኛል ፡ ያልኩት
የአንበሶችን ፡ አፍ ፡ ቆልፎ ፡ አየሁት (፪x)
ንጉስ ፡ ሆይ ፡ ልንገርህ ፡ አምላኬ ፡ ጀግና ፡ ነው
ታምርን ፡ ለማድረግ ፡ በስሙ ፡ ቀላል ፡ ነው ፡ ለጌታ ፡ ቀላል ፡ ነው

አዝነጋ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ (፪x)
በሰላም ፡ አደርኩኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ
እንደመሸ ፡ አልቀረም ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ
በሰላም ፡ አደርኩኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ
አንበሶች ፡ አልበሉኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ

ውስጤ ፡ ነገር ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ ያስቀመጠው
ባስጨነቀህ ፡ ነገር ፡ መፍትሄ ፡ በኔ ፡ አለ (፪x)
መቃብሬ ፡ ጉድጉዓድ ፡ ባንበሶች ፡ ማደሪያ
በፍፁም ፡ አይሆንም ፡ አለው ፡ ብዙ ፡ ሥራ (፪x)

አዝነጋ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ (፪x)
በሰላም ፡ አደርኩኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ
እንደመሸ ፡ አልቀረም ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ
በሰላም ፡ አደርኩኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ
አንበሶች ፡ አልበሉኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ

ባለራእይ ፡ ነኝ ፡ አልበላን ፡ አንበሳ
ሰላም ፡ አድረያለሁ ፡ ብአርሱ ፡ የተነሳ ፡ ከጌታ ፡ የተነሳ
አላሳፈረንም ፡ ያመንኩት ፡ ጌታን ፡ ነው
በላተኛው ፡ ትራስ ፡ ሆኖኝ ፡ አይቻለሁ (፪x)

የዳንኤል ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ይህን ፡ ሁሉ ፡ የሰራው
ሌሊቱ ፡ ነግቶልናል ፡ ተራው ፡ የኔ ፡ ነው (፪x)

ባለራዕይ ፡ ነኝ ፡ ተራው ፡ የኔ ፡ ነው
ውስጤ ፡ ነገር ፡ አለ ፡ ተራው ፡ የኔ ፡ ነው
በፍፁም ፡ አልሞትም ፡ ተራው ፡ የኔ ፡ ነው
ያወርሰናል ፡ ጌታ ፡ ተራው ፡ የኔ ፡ ነው
ተራው ፡ የኔ ፡ ነው ፡ ተራው ፡ የኔ ፡ ነው