መንግሥቱን ፡ ሕዝቡን ፡ ጠብቅ (Mengistun Hizbun Ttebiq)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

መንግሥቱን ፡ ሕዝቡን ፡ ጠብቅ ፡ ኦ! አምላክ
በረከት ፡ አውርድ ፡ በሃገሩ ፡ ላይ
ፍቅሩ ፡ ይግዛነ ፡ ሰላሙ ፡ ይልማ
ጨለማ ፡ ይብራ ፡ በጽድቁ ፡ ፀሃይ

ጌታና ፡ ሎሌን ፡ ቤትና ፡ ጐጆን
ጠብቅ ፡ በእጅህ ፡ ከሁሉ ፡ ጉዳት
በቀና ፡ መንገድ ፡ አንተ ፡ ምራነ
ፍጠር ፡ በልባችን ፡ ቅዱስ ፡ ቅናት

የወንጌል ፡ ዕውቀት ፡ ባገሩ ፡ ይስፋ
አካፍለነ ፡ ነዋሪ ፡ ደስታን
አርበኞች ፡ ሁነን ፡ ድል ፡ ልንነሣ
መንግሥትህን ፡ ልንወርሰው ፡ አብቃን