ምን ፡ ተስኖት (Men Tesenot)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ደረቁን ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ምን ፡ ተስኖት
የሞላዋል ፡ በአበባ ፡ ምን ፡ ተስኖት
የጐደለኝን ፡ ሁሉ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ያደርግልኛል ፡ ሙሉ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ለእርሱ ፡ የሚያቅት ፡ የለም
ይችላል ፡ እርሱ ፡ ዘለዓለም (፪x)
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነውና
እናክብረው ፡ በምሥጋና

የሞተውን ፡ እሬሳ ፡ ምን ፡ ተስኖት
እናያለን ፡ ሲያስነሳ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ለእኛ ፡ ያቃተን ፡ ሁሉ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ይቻለዋል ፡ ለእርሱ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ኤልሻዳይ ፡ አምላክ ፡ ነውና
የሚሳነው ፡ የለምና
ምን ፡ ተስኖት ፡ እንበለው (፪x)
ድል ፡ የሚገኘው ፡ ያኔ ፡ ነው

ጐልያድን ፡ የዘረረ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ባሕሩንም ፡ የከፈለ ፡ ምን ፡ ተስኖት
የፈርኦንን ፡ ሠራዊት ፡ ምን ፡ ተስኖት
አርጐታል ፡ የውኃ ራት ፡ ምን ፡ ተስኖት
ከአቅማችን ፡ በላይ ፡ ከብዶ
የሚረዳን ፡ ወገን ፡ ጠፍቶ
ምን ፡ ተስኖት ፡ ግን ፡ ይደርሳል (፪x)
ከጐናችን ፡ ሆኖ ፡ ይቆማል

ደምና ፡ ባይታይም ፡ ምን ፡ ተስኖት
ነፋስም ፡ ባይነፍስ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ሸለቆውን ፡ በውሃ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ይሞላዋል ፡ የእኛ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ለሰው ፡ የማይቻለው
ለእርሱ ፡ ብቻ ፡ የተቻለው
ሁሉን ፡ ነገር ፡ ያደርጋል (፪x)
ምን ፡ ተስኖት ፡ ይቻለዋል