መልክህን ፡ ጌታዬ (Melkehen Gietayie)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

መልክህን ፡ ጌታዬ ፡ ፀሐይ ፡ አክስሎታል
በሐሩሩ ፡ ብዛት ፡ ከስተህ ፡ ገርጥተሐል
ምቾትም ፡ ድሎትም ፡ አልነበረውም ፡ ጌታ
ሰብአዊ ፡ ፍጡር ፡ በውርደት ፡ ተመታ (፪x)

የሞት ፡ ጽዋ ፡ ቀርባ ፡ ፈዋሼ ፡ ሲጨነቅ
የአባቱ ፡ ድምጽ ፡ ርቆት ፡ በጭንቀት ፡ ሲማቅቅ
አንጀቱ ፡ ተጣብቆ ፡ አጥንቱ ፡ ሰልስሎ
የእኔን ፡ ሕይወት ፡ ዋጀ ፡ ጌታዬ ፡ ተጋድሎ (፪x)

ተራራ ፡ አይቧጠጥክ ፡ በመዳህ ፡ ስትወጣ
ሆንክልኝ ፡ መድህኔ ፡ ስለእኔ ፡ ከርታታ
ለአንተ ፡ የጣር ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ የፈውስ ፡ እለት
እራስህን ፡ አጋልጠህ ፡ ፈጸምከው ፡ በትዕግሥት (፪x)