መድኃኒት ፡ ተገኘልን (Medhanit Tegegnelen)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

መድኃኒት ፡ ተገኘልን ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ደም
ከአምላክ ፡ ጋራም ፡ ዕርቅ ፡ ተደረገልን
ለምንስ ፡ እንጨነቅ? አገኘን ፡ ሰላም
የጥል ፡ ግድግዳም ፡ ፍፁም ፡ ፈረሰልን
አሁንስ ፡ ቀኑ ፡ ነጋ ፡ ሌሊትም ፡ አልፏል
ተማረከ ፡ ኃይለኛው ፡ ምርኮኛውም ፡ ይፈታል
በክርስቶስ ፡ መስቀል ፡ አምላክ ፡ ታረቀነ

አምላክ ፡ ከታረቀኝም ፡ በኢየሱስ ፡ ልጁ ፡ ነኝ
ልጅነት ፡ ተዋጀልኝ ፡ በሕማሙ
ኦ! አምላኬ ፡ በክርስቶስ ፡ ከጥንት ፡ ከወደድኸኝ
የመንግሥትህ ፡ ወራሽ ፡ ነኝ ፡ ስለስሙ
በባሪያ ፡ መንፈስ ፡ ተይዤ ፡ ለጽድቅ ፡ የማሰንሁ
የፀጋህን ፡ ሥጦታ ፡ ልገዛው ፡ ያሰብሁ
እኔ ፡ በኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ልጅህ ፡ ሆንሁ

ምንደኞች ፡ ሆነን ፡ ሠርተን ፡ ደመወዝን ፡ ብናገኝ
ልጅነት ፡ አናገኝም ፡ በሥራችን
መድኃኒት ፡ ሆይ ፡ በጽድቅህ ፡ አንተ ፡ ካጸደቅኸኝ
አሮጌ ፡ ጨርቅ ፡ አያርክስ ፡ አዲስ ፡ ልብሴን
እኔ ፡ ሁለንተናዬ ፡ ፍፁም ፡ የረከስሁ
በአንተ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ፍፁም ፡ ተቀደስሁ
የራሴን ፡ ጽድቅ ፡ ከጉድፍ ፡ ልቁጠረው

ፊት ፡ ኃጢአቱን ፡ ነቅሎ ፡ ጽድቁንም ፡ ፈጽሞ
ኋላም ፡ በጽድቁ ፡ አንተን ፡ የሚፈልግ
ምሕረትህ ፡ የሚገባው ፡ ሊሆን ፡ ተዳክሞ
በራሱ ፡ አቅም ፡ ተስፋ ፡ የሚያደርግ
ያ ፡ ምስኪን ፡ ሰው ፡ ይስታል ፡ ጽድቅንም ፡ አጥቶ
ምሕረትህንም ፡ ያጣል ፡ ወደ ፡ አንተም ፡ መጥቶ
በጽድቅህ ፡ ጽድቁን ፡ ሊያገኝ ፡ አይቻለውም

ኃጥአንን ፡ ሁሉ ፡ እንጂ ፡ ጻድቃንን ፡ ለመጥራት
መድኃኒታችን ፡ ወደዚህ ፡ አልመጣም
የታመመው ፡ ሳይድንም ፡ መድኃኒት ፡ ለመሻት
ቢቀርብ ፡ በሐኪም ፡ ከቶ ፡ አልተቀጣም
እኔም ፡ ኦ! ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መጥቼ
የፈለግሁትን ፡ ሁሉ ፡ በከንቱ ፡ አግኝቼ
በደስታ ፡ ቅዱስ ፡ ስምህን ፡ ላመስግን

ዓለምም ፡ ሳይመሠረት ፡ በምሕረትህ ፡ ፈቃድ
ልጅህ ፡ ልሆን ፡ በኢየሱስ ፡ መርጠኸኛል
ሥምረትህም ፡ ኦ! አምላክ ፡ አሁን ፡ እንዴት ፡ ይካድ
በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሁሉን ፡ ሰጥተኸኛል
የምክርህን ፡ ምሥጢር ፡ በቃልህ ፡ ገለጥኸው
የሰው ፡ ምዳን ፡ አምላክ ፡ በፀጋ ፡ ብቻ ፡ ነው
እኔም ፡ በፀጋህ ፡ ብቻ ፡ እመካለሁ