ለክብርህ ፡ አብቃኝ (Lekibrih Abqagne)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ያልተገረዘ ፡ ሸለፈት
ክፉ ፡ ዕንቅፋት ፡ ነው ፡ በዕውነት
ለክርስትና ፡ ሕይወት

ስለዚህ ፡ ጌታ ፡ ግረዝና
ለክብርህ ፡ አብቃኝ ፡ አውብና
በሕይወቴ ፡ ውስጥ ፡ የምታየው
ልብህን ፡ በጣም ፡ ያሳዘነው

አዝ፦ ያልተገረዘ ፡ ሸለፈት
ክፉ ፡ ዕንቅፋት ፡ ነው ፡ በዕውነት
ለክርስትና ፡ ሕይወት

ይቆረጥ ፡ ዛሬ ፡ በሥልጣንህ
ፈቅጃለሁና ፡ ይኸውልህ
እራሴን ፡ በፊትህ ፡ አቅርቤአለሁ
ሙሉ ፡ ሕይወቴን ፡ እሰጣለሁ

አዝ፦ ያልተገረዘ ፡ ሸለፈት
ክፉ ፡ ዕንቅፋት ፡ ነው ፡ በዕውነት
ለክርስትና ፡ ሕይወት

እንደምትወድ ፡ ግረዝና
ከአንተ ፡ በሆነው ፡ ቅድስና
አጥበህ ፡ አንጽተህ ፡ አስተካክለኝ
ፀሎቴ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ተቀበለኝ

አዝ፦ ያልተገረዘ ፡ ሸለፈት
ክፉ ፡ ዕንቅፋት ፡ ነው ፡ በዕውነት
ለክርስትና ፡ ሕይወት

ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ! በእኔ ፡ ሕይወት
ተቀበልና ፡ ክበርበት
ምራው ፡ ሕይወቴን ፡ በፈቃድህ
ዛሬ ፡ ወድጄ ፡ ሳስረክብህ

አዝ፦ ያልተገረዘ ፡ ሸለፈት
ክፉ ፡ ዕንቅፋት ፡ ነው ፡ በዕውነት
ለክርስትና ፡ ሕይወት