ለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ልትዋጅ (Lealem Hiyot Litwaj)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ልትዋጅ
ሥጋችንን ፡ የለበስክህ
ተስፋችንን ፡ ልታዘጋጅ
ኦ ! ኢየሱስ ፡ ሞትን ፡ ቀመስኽ
ያለአንተ ፡ ግን ፡ በጠፋነ
ሲዖል ፡ ተከፈተብነ
ሞትም ፡ ርስታችን ፡ ነበር

አንተም ፡ ስታይ ፡ የእኛን ፡ ጉዳት
በፍቅር ፡ ራራህልን
ልታድነነም ፡ ከጥፋት
ወዳለም ፡ ወረድህልን
ከአንተ ፡ ሞትና ፡ ሕማም
የእግዚአብሔር ፡ ሰላም
ኦ! ኢየሱስ ፡ ተገኘልን

በትሩፋትህ ፡ አምነን
ወዳምላክ ፡ ስንመጣ
ምሉ ፡ ይቅርታ ፡ ሰጠኸን
በሕግ ፡ እንዳንቀጣ
እኛም ፡ ይህን ፡ ተቀብለን
በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ ታምነን
ከሞት ፡ እንድናለን

ቸር ፡ ወንድማችን ፡ አንተ ፡ ነህ
እንዴት ፡ አክብረኸናል
ዘለዓለም ፡ ከኛ ፡ ጋራ ፡ ነህ
ሁሉንም ፡ ሰጥተኸናል
የዓለም ፡ ስድብና ፡ ጥል
ከቶ ፡ ሊጐዳን ፡ እንዳይችል
አምባችን ፡ ያምላክ ፡ ልጅ ፡ ነው

ግሩም ፡ ፀጋህን ፡ የሰጠኸን
መድኃኒት ፡ ሆይ ፡ ተወደስ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ልጆች ፡ ነን
ኦ! ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
አምላክን ፡ እናመስግንም
እርሱ ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ስም
ቸር ፡ አባታችን ፡ ሆነ