ለአምላክ ፡ በሰማይ ፡ ቀኙ (Lamlak Besemay Qegnu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ለአምላክ ፡ በሰማይ ፡ ቀኙ
ሕዝቦች ፡ ሁሉ ፡ ይስገዱ
ድምፅ ፡ ያለበት ፡ ነፍስ ፡ ሁሉ
ያመስግን ፡ በመቅደሱ

በእጁ ፡ የፈጠረው
እጅግ ፡ ግሩምና ፡ መልካም ፡ ነው
ከዘለዓለም ፡ ያሳየው
ተገልጦልን ፡ ግርማው

ከአምላክ ፡ ላስታረቀን
ከጥፋት ፡ ለነጠቀን
እንደ ፡ አባት ፡ ላሞገሰን
እንዘምር ፡ ሁሉ ፡ ቀን

ፍጥረቱ ፡ በመላዋ
ስብሓት ፡ ታቅርብ ፡ ለጌታ
ነፍሴም ፡ ደግሞ ፡ በደስታ
ታመስግን ፡ ሃሌሉያ