ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው (Laderegihligne Yemimelisew)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አንደበት ፡ የለኝ ፡ ስምህን ፡ ልጠራ
ምላሥም ፡ የለኝ ፡ ሥራህን ፡ ላወራ
ልናገርም ፡ ብል ፡ ጊዜው ፡ አይበቃ
ተመስገን ፡ ብዬ ፡ በአጭሩ ፡ ላብቃ ።

ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ እጄ ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ የአፌን ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና ።

በፍቅር ፡ ቃልህ ፡ ልቤን ፡ ስትመታ
ነፍሰ ፡ ሥጋዬን ፡ ከእሥር ፡ ልትፈታ
ምን ፡ አለኝና ፡ ምንን ፡ ልክፈልህ?
ከተቀበልኸኝ ፡ ክበር ! ልበልህ ።

ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ እጄ ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ የአፌን ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና ።

ከትቢያ ፡ አንስተህ ፡ ሰው ፡ ስታደርገኝ
በነፍስ ፡ በሥጋ ፡ ስትባርከኝ
ሰማያዊ ፡ ፍቅርህ ፡ ልቤን ፡ ሲሞላ
ተመስገን ፡ እንጂ ፡ የለኝም ፡ ሌላ ።

ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ እጄ ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ የአፌን ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና ።