ሕዝቦች ፡ ሁሉ ፡ ተደሰቱ (Hezboch Hulu Tedesetu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሕዝቦች ፡ ሁሉ ፡ ይደሰቱ ፡ አምላክን ፡ ያወድሱ
የቆማችሁ ፡ በኪዳኑ ፡ በአንድነት ፡ ቅረቡ
ቅረቡ ፡ በዕልልታ ፡ ዘምሩ ፡ ለቸር ፡ ጌታ (፪x)

እርሱ ፡ ነው ፡ የፈጠረነ ፡ ልጆቹን ፡ የጠራነ
የጠፉትንም ፡ ያዳነ ፡ እስካሁን ፡ ያቆመነ
እርሱ ፡ በሰማይ ፡ ደስታ ፡ ሊያገባነ ፡ በተስፋ (፪x)

ዘምሩ ፡ አገልጋዮቹ ፡ ወድሱት ፡ በመቅደሱ
ከአገር ፡ ሁሉ ፡ ተከማቹ ፡ ለአባታችን ፡ ስገዱ
ርኅሩህ ፡ ሆኖ ፡ ይጸናል ፡ እስከ ፡ ሞት ፡ ይመራናል (፪x)