ገብተናል ፡ በአምላክ ፡ መቅደስ (Gebtenal BeAmlak Meqdes)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ገብተናል ፡ በአምላክ ፡ መቅደስ
ግርማውን ፡ በሚያሳይ
እንስገድ ፡ በቀና ፡ መንፈስ
ለአባታችን ፡ በሰማይ
ጸሎታችንን ፡ ይሰማል
ፀጋን ፡ ምሕረትን ፡ ይሰጣል

መጥቼ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እኔ
ቸር ፡ አባት ፡ ተቀበለኝ
ይሁን ፡ መቅደስህ ፡ በልቤ
ከክፋቱ ፡ አንጻልኝ
አስርጽበት ፡ ቅድስና
ምላበት ፡ የአንተን ፡ ብፅዕና

ልቤን ፡ አድርግ ፡ ፍሬያማ ፡ እርሻ
ቅዱስ ፡ ዘር ፡ ሲዘራበት
ጨለማን ፡ በልቤ ፡ አብራ
ስጥ ፡ በስብከት ፡ በረከት
በመስማቴ ፡ ከበጐነት
ፍሬን ፡ ላፈራ ፡ ለአንተ ፡ ክብረት

እሰማለሁ ፡ ጌታ ፡ እዘዝ
ትዕዛዝህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ሲፈስስ
የማይረካ ፡ ይጠፋል
መግበን ፡ በቸርነት
አድነን ፡ ከሁሉ ፡ ጭንቀት