ፍቅርን ፡ አስተማረን (Fiqrin Astemaren)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ጠላቶችን ፡ እንድንወድ ፡ ጌታ ፡ አስተማረን
በመስቀል ፡ ተቸንክሮ ፡ ፍቅሩን ፡ ገለጸልን
መልካም ፡ ፍቅር ፡ ኦ! መልካም ፡ ፍቅር
ተወለደ ፡ ሊጠላ ፡ ለእኛ ፡ በመስቀል ፡ ለመሰቀል
ያዳምን ፡ ልጆች ፡ ኃጢአት ፡ በደሙ ፡ ለመክፈል (፪X)

መድኅኔ ፡ አስተምሮኛል ፡ በፍቅር ፡ እንድመራ
ያዘነን ፡ እንዳጽናና ፡ ላጣው ፡ እንድራራ
ይገባኛል ፡ ኦ! ልታዘዘው
እርሱ ፡ የእኔን ፡ መከራ ፡ ችሎ ፡ ሞቶአልና ፡ ሞቶአልና
ይገባኛል ፡ እኔም ፡ ልጓዝ ፡ በእርሱ ፡ ጐዳና ፡ (፪X)

በምድር ፡ የምናያቸው ፡ ሁሉም ፡ ይጠፋሉ
ዕምነት ፡ ተስፋዬ ፡ ፍቅር ፡ ጸንተው ፡ ይኖራሉ
ጌታ ፡ ያዛል ፡ እንድንዋደድ
ጌታ ፡ ነፍሱን ፡ ለእኛ ፡ እስኪሰጥ ፡ አፍቅሮናል ፡ አፍቅሮናል
እርስ ፡ በርሳችን ፡ ልንዋደድ ፡ ይገባናል ፡ (፪X)

ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ ክበር ፡ መድኃኒቴ
በሰማያዊ ፡ ፍቅር ፡ ዳበረ ፡ ሕይወቴ
ሃሌ ሉያ ! ኦ! ለጌታዬ
በለመለመ ፡ መስክ ፡ ኢየሱስ ፡ ይመራኛል ፡ ይመራኛል
በየዕለቱ ፡ የጌታ ፡ ፍቅር ፡ ይታየኛል (፪X)