ፍቅር ፡ ከላይ (Fiqr Kelay)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ ፣
ፍቅር ፡ ከላይ ፣ ፍቅር ፡ ከላይ
ፍቅር ፡ ከላይ ፡ ከአባታችን ፡ (፪X)
በራሱ ፡ ደም ፡ አስታረቀን ።

በኃጢአት ፡ የጠፋ ፡ ዓለም
ከጥንት ፡ ከሔዋን ፡ ከአዳም
ገዝቶት ፡ የጨለማው ፡ ሥልጣን
ኢየሱስ ፡ ሲመጣ ፡ ይበራል ።

አዝ ፣
ፍቅር ፡ ከላይ ፣ ፍቅር ፡ ከላይ
ፍቅር ፡ ከላይ ፡ ከአባታችን ፡ (፪X)
በራሱ ፡ ደም ፡ አስታረቀን ።

በውርደቱ ፣ እኛ ፡ ከብረናል
በሞቱ ፣ ተለውጠናል
በትንሣዔው ፡ ተነሥተናል
በቁስሉ ፡ ተፈውሰናል ።

አዝ ፣
ፍቅር ፡ ከላይ ፣ ፍቅር ፡ ከላይ
ፍቅር ፡ ከላይ ፡ ከአባታችን ፡ (፪X)
በራሱ ፡ ደም ፡ አስታረቀን ።

ከጠላት ፡ ቤት ፡ አምልጠናል
በብርሃን ፡ ተመላልሰናል
ሥጦታን ፡ አፍስሶልናል
ወደ ፡ ቤቱም ፡ ይወስደናል

አዝ ፣
ፍቅር ፡ ከላይ ፣ ፍቅር ፡ ከላይ
ፍቅር ፡ ከላይ ፡ ከአባታችን ፡ (፪X)
በራሱ ፡ ደም ፡ አስታረቀን ።

ጠላቶች ፡ ነበርን ፣ ታርቀናል
ወራሽ ፡ ልጆቹ ፡ አድርጐናል
ሠልፍ ፡ ውጊያን ፡ አስተምሮናል
እኛም ፡ ብዙዎችን ፡ ማርከናል

አዝ ፣
ፍቅር ፡ ከላይ ፣ ፍቅር ፡ ከላይ
ፍቅር ፡ ከላይ ፡ ከአባታችን ፡ (፪X)
በራሱ ፡ ደም ፡ አስታረቀን ።