ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ስለ ፡ እኛ ፡መከራ ፡ ተቀበለ (Eyesus Kristos Sile Egna Mekera Teqebele)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ስለ ፡ እኛ
መከራ ፡ ተቀበለ
እርሱም ፡ እንደ ፡ በደለእኛ
በእንጨት ፡ ላይ ፡ ተሰቀለ
ቤዛ ፡ እርሱ ፡ ሆኗል
በኛም ፡ ፈንታ ፡ ሙቷል

በሕማማቱ ፡ በሞቱም
ምሕረት ፡ ተዋጅቶልናል
በትንሣዔውም ፡ በሕይወቱም
ጽድቅም ፡ ተገኝቶልናል
በዕርገቱም ፡ ወደ ፡ ላይ
ሥፍራ ፡ ሰጠን ፡ በሰማይ

በመድኃኒታችን ፡ መስቀል
የሚያምን ፡ ምሥጉን ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስን ፡ መቀበል
የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ነው
የመድኃኒታችን ፡ ሞት
ለእኛ ፡ ነው ፡ ብጹዕ ፡ ሕይወት