እንደሎጥ ፡ እንደኖኅ ፡ ዘመን (EndeNoh EndeLott Zemen)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ ፣
እንደሎጥ ፡ እንደኖኅ ፡ ዘመን
ኃጢአትን ፡ እጅግ ፡ አበዛን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ ገሥፀን
አባት ፡ ነህና ፡ ቆንጥጠን
ስንጠፋ ፡ ዝም ፡ አትበለን (፪X)

ልባችንን ፡ የመንፈስህ ፡ ማደሪያው
ኃጢአት ፡ አሻገተው
መቅደስህን ፡ ተነሥ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አጽዳው
ሥጋችንን ፡ ቅጣው

አዝ ፣
እንደሎጥ ፡ እንደኖኅ ፡ ዘመን
ኃጢአትን ፡ እጅግ ፡ አበዛን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ ገሥፀን
አባት ፡ ነህና ፡ ቆንጥጠን
ስንጠፋ ፡ ዝም ፡ አትበለን (፪X)

ደግመህ ፡ ደግመህ ፡ ስቀለው ፡ ሥጋችንን
እንምሰልህ ፡ አንተን
በመንፈስህ ፡ የጀመርነው ፡ ጉዞአችን
ለሕይወት ፡ ይሁንልን

አዝ ፣
እንደሎጥ ፡ እንደኖኅ ፡ ዘመን
ኃጢአትን ፡ እጅግ ፡ አበዛን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ ገሥፀን
አባት ፡ ነህና ፡ ቆንጥጠን
ስንጠፋ ፡ ዝም ፡ አትበለን (፪X)

ቅዱስ ፡ ስምህን ፡ አረግነው ፡ መነገጃ
ብር ፡ ወርቅን ፡ ማትረፊያ
መኖራችን ፡ ነበር ፡ ለዓለም ፡ ብርሃን
ጨለማ ፡ ሆነናል

አዝ ፣
እንደሎጥ ፡ እንደኖኅ ፡ ዘመን
ኃጢአትን ፡ እጅግ ፡ አበዛን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ ገሥፀን
አባት ፡ ነህና ፡ ቆንጥጠን
ስንጠፋ ፡ ዝም ፡ አትበለን (፪X)

በሰናዖር ፡ ግንባችንን ፡ ሠርተናል
እጅግ ፡ ተኩራርተናል
ኃጢአት ፡ ለብሰን ፡ ዓመጻን ፡ ደርበናል
ፈውስ ፡ ያስፈልገናል

አዝ ፣
እንደሎጥ ፡ እንደኖኅ ፡ ዘመን
ኃጢአትን ፡ እጅግ ፡ አበዛን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ ገሥፀን
አባት ፡ ነህና ፡ ቆንጥጠን
ስንጠፋ ፡ ዝም ፡ አትበለን (፪X)