ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ጌታ (Dinq Niew Lenie Gieta)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

[ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ጌታ
ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ኢየሱስ
ሞኝነት ፡ ቢመስላት ፡ ለዓለም
ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ዘለዓለም] ፪X

አሥራ ፡ ሁለት ፡ ዓመት ፡ ደም ፡ ሲፈሰኝ ፡ ኖሬ
ሠላሳ ፡ ስምንት ፡ ዓመት ፡ እግሮቼን ፡ ታስሬ
ዛሬ ፡ ተፈወስኩኝ ፡ ቀሚሱን ፡ ዳስሼ
ይኸው ፡ እዘላለሁ ፡ በሥሙ ፡ ታድሼ

[ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ጌታ
ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ኢየሱስ
ሞኝነት ፡ ቢመስላት ፡ ለዓለም
ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ዘለዓለም] ፪X

ግንበኞች ፡ የናቁት ፡ የማዕዘን ፡ እራስ
ለእኔ ፡ ግን ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ውዴ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ብዙዎች ፡ ያጥላሉታል ፡ ርካሽ ፡ ዕቃ ፡ አድርገው
ለእኔ ፡ ለደካማው ፡ ኢየሱስ ፡ ድንቅ ፡ ነው

[ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ጌታ
ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ኢየሱስ
ሞኝነት ፡ ቢመስላት ፡ ለዓለም
ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ዘለዓለም] ፪X

ሞኝ ፡ ነህ ፡ ይሉኛል ፡ ሳይረዱት ፡ ቀምሰው
ተመለስ ፡ ይሉኛል ፡ ዋጋ ፡ ቢስ ፡ አደርገው
አልፈልግም ፡ ካልኩኝ ፡ ጭቅጭቅ ፡ ምንድነው?
እንቢ ፡ አሻፈረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ድንቅ ፡ ነው

[ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ጌታ
ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ኢየሱስ
ሞኝነት ፡ ቢመስላት ፡ ለዓለም
ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ዘለዓለም] ፪X

ገንዘብም ፡ ውድ ፡ ነው ፡ ውበትም ፡ ድንቅ ፡ ነው
ለእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ እንጂ ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው
እጅህ ፡ ምሥኪን ፡ ድሃ ፡ ታናሽ ፡ ሰው ፡ እመስላለሁ
ዕጹብ ፡ ድንቅ ፡ ውድ ፡ ዕቃ ፡ ኢየሱስን ፡ ይዣለሁ

[ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ጌታ
ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ኢየሱስ
ሞኝነት ፡ ቢመስላት ፡ ለዓለም
ድንቅ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ዘለዓለም] ፪X