ቸሩ ፡ አባት ፡ መድኃኒታችን (Cheru Abat Medhanitachen)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ቸሩ ፡ አባት ፡ መድኃኒታችን
በፀጋህ ፡ ኃይል ፡ ወደ ፡ እኛ ፡ ና
በልጆችህ ፡ መካከል ፡ ደግሞ
የመንፈስህን ፡ ብርሃን ፡ አብራ

ኢየሱስ ፡ አሁን ፡ ወደ ፡ ሁላችን
ና ፡ ና ፡ በፍቅርህ ፡ አሙቀን
የራሴን ፡ ኃጢአት ፡ ግለጽልኝ
ወደ ፡ አንተ ፡ እንድሸሽ ፡ አሁን

ምሥጋና ፡ ኃይል ፡ ውዳሴ
ክብር ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ይገባል
በቃልህም ፡ እንድጸና ፡
በፍቅርህ ፡ ፀጋህን ፡ ስጠን