Classics/Bel Efer Telatie

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


|ርዕስ=በል ፡ እፈር ፡ ጠላቴ |Title=Bel Efer Telatie |ቋንቋ=አማርኛ |Language=Amharic |Lyrics=የመጎብኛዬ ፡ ወራት ፡ ሲመጣ ለሚፈሩህ ፡ የጽድቅ ፡ ፀሐይ ፡ ደግሞ ፡ ሲወጣ ፀሎቴም ፡ ተሰማ ጠላት ፡ እየሰማ ዕዳዬ ፡ ተከፈለ ከሳሼ ፡ የታለ ጉልበቴ ፡ በረታ በኢየሱስ ፡ ጌታ

አዝ፦ በል ፡ እፈር ፡ ጠላቴ ፡ እዳዬ ፡ ተከፍሏል

ከየት ፡ ታምጣ ፡ ከሳሼ ፡ ቀንበሬ ፡ ተሰብሯል
በነጻነት ፡ ልኖር ፡ ነጻ ፡ አውጥቶኛል
ዳግም ፡ ላልታሰር ፡ ኤፍታ ፡ ብሎ ፡ ለቆኛል

ክብር ፡ ለስሙ ፡ ይሁን ክብር ፡ ላዳነኝ ፡ ይሁን ክብር ፡ ለጌታ ፡ ይሁን ክብር ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን

1. ዝናብም ፡ ባይኖር ፡ ነፋስም ፡ ባላይ

ድል ፡ አውጃለሁ ፡ ባዶ ፡ ተስፋ ፡ ላይ
ደረቁ ፡ ምድር ፡ ይለመልማል
በባዶ ፡ ጉድጓድ ፡ ዉሃ ፡ ይሞላል
ያለቀው ፡ ነገር ፡ ሞልቶ ፡ ይፈሳል
የተጠማ ፡ ሁሉ ፡ ጠጥቶ ፡ ይረካል

2. ምንም ፡ ቢበዛ ፡ የኔ ፡ መከራ

ከቶ ፡ ቢጎድል ፡ የወይራ ፡ ሥራ
ያዳነኝ ፡ ጌታ ፡ ሀይል ፡ ይሆነኛል
እንደ ፡ ዋላ ፡ እግሬን ፡ ያበረታኝል
ጠባቂዬ ፡ የሱስ ፡ አቅም ፡ ይሆነኛል
በከፍታ ፡ ላይ ፡ ያራምደኛል

3. ያመንኩት ፡ ወዳጅ ፡ ቢከዳ ፡ እንኳን

ቢፈርስ ፡ ቢበተን ፡ ምድራዊ ፡ ድንኳን
የታመንኩ ፡ ጌታ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ያለው
ያረጀውን ፡ ነገር ፡ አዲስ ፡ ጀመረው
ማይከዳ ፡ ወዳጅ ፡ ከጎኔ ፡ ያለው
የታሪክ ፡ መዝገብ ፡ አገላበጠው
ያመንኩት ፡ የሱስ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ያለው
የሞትን ፡ አዋጅ ፡ ገለባበጠው

ሞቶ ፡ ተቀብሮ ፡ ቢሸት ፡ ነገሬ አንድም ፡ ባይሰማ ፡ አስደሳች ፡ ወሬ ወድቆ ፡ አይቀርም ፡ በከንቱ ፡ ሞቶ ሕይወት ፡ ይዘራል ፡ ጌታዬ ፡ መጥቶ ትንሣኤ ፡ አለ ፡ ዛሬም ፡ ካባቴ በእግሩ ፡ ቆሟል ፡ እፈር ፡ ጠላቴ

አዝ፦ በል ፡ እፈር ፡ ጠላቴ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁ

ቢጨልምብኝም ፡ ብርሃን ፡ እወጣልሁ
ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ እመለከታለሁ
መድኃኒቴን ፡ አምላክ ፡ ተስፋ ፡ አደርጋለሁ
እሱም ፡ ይሰማኛል ፡ ጽድቅን ፡ ያሳየኛል
እሱም ፡ ያደምጠኛል ፡ እረፍት ፡ ይሰጠኛል

}}