በበረሃ ፡ ስጓዝ ፡ ጉዳት ፡ ቢደርስብኝ (Bebereha Sguaz Gudat Bidersibigne)
From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ እላለሁኝ
እኔ ፡ ማዳኑን ፡ ስላየሁኝ
በበረሃ ፡ ስጓዝ ፡ ቢደርስብኝ ፡ ጉዳት
ረሃብና ፡ ጥማት ፡ ሕይወቴን ፡ ሲይዛት
ማነው ፡ ያዘነልኝ? ወድቄ ፡ እንዳልቀር
የደገፈኝ ፡ ማነው ፡ እንዳልሰባበር?
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ እላለሁኝ
እኔ ፡ ማዳኑን ፡ ስላየሁኝ
በመከራ ፡ ሥቃይ ፡ ነፍሴ ፡ ስትጨነቅ
ልቤ ፡ በፍርሃት ፡ በሃዘን ፡ ሲጥለቀለቅ
በድካም ፡ ተይዤ ፡ ወጀብ ፡ ሲያንገላታኝ
በቃልህ ፡ ታምኜ ፡ እንድቆም ፡ አረግኸኝ
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ እላለሁኝ
እኔ ፡ ማዳኑን ፡ ስላየሁኝ
ጠልቀው ፡ በማያውቁት ፡ ውስጣዊ ፡ ሕይወቴን
ሲያወጉ ፡ እየሰማሁ ፡ የእኔን ፡ ከንቱነቴን
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ድልን ፡ሰጠኸኝ
ደካማ ፡ ምስኪኑን ፡ ለክብርህ ፡ አቆምኸኝ
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ እላለሁኝ
እኔ ፡ ማዳኑን ፡ ስላየሁኝ
|