በአፋችሁም ፡ በልባችሁም ፡ ክርስቶስን ፡ አመስግኑ (Beafachum Belibachihum Kristosn Amesginu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በአፋችሁም ፡ በልባችሁም
ክርስቶስን ፡ አመስግኑ
ስለ ፡ እኛ ፡ ሙቶ ፡ ተኛ
ሦስት ፡ ቀን ፡ በመቃብሩ
ከመቃብር ፡ በአምላክ ፡ ክብር
ለተነሣው ፡ ዘምሩ

ስለ ፡ ዕዳችን ፡ ተቀጣልን
ጽድቁንም ፡ አወረሰን
ያ ፡ ረጃችን ፡ ከጭንቃችን
ለዘለዓለም ፡ አዳነን
በሞት ፡ ፈንታ
ሕይወት ፡ ጸንታ
ለእኛም ፡ ሕይወት ፡ ሰጠን

እኛን ፡ ምሮ ፡ ሞትን ፡ ሽሮ
ሰይጣንን ፡ ቀጠቀጠ
ኃይልም ፡ ሁሉ
በዓለም ፡ ምሉ
ለወልድ ፡ ብቻ ፡ ተሰጠ
በብርሃኑ ፡ ለኃጥአኑ
ምሕረትም ፡ ተገለጠ

ለዓብ ፡ ክብር ፡ በዚህ ፡ ምድር
የሰው ፡ ውዳሴ ፡ ይሁን
ላንዱ ፡ ልጁም ፡ እንደዚሁም
 እናመስግን ፡ ምሕረቱን
ለቸር ፡ ውዱስመንፈስ ፡ ቅዱስ
እናሳርግ ፡ ውዳሴውን