በክርስቶስ ፡ ቁስል ፡ ውስጥ ፡ ልረፍ (BeKiristos Qusil Wustt Liref)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በክርስቶስ ፡ ቁስል ፡ ውስጥ ፡ ልረፍ
ከአምላክ ፡ መቅሠፍትም ፡ ልትረፍ
የክርስቶስ ፡ ሞትና ፡ ሕማም
ለነፍሴ ፡ ነው ፡ ብጹዕ ፡ ሰላም

ስቀርብም ፡ ወደ ፡ አምላክ ፡ ፍርድ
የክርስቶስ ፡ ደም ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ዕርድ
ምዕመን ፡ ከዓለም ፡ ሲለያይ
ይወርሳል ፡ ሕይወት ፡ በሰማይ

ሞት ፡ ሆይ! የት ፡ ነው ፡ ማሸነፍህ?
ልረግ ፡ ወደ ፡ አምላክ ፡ በክንፍህ
የክርስቶስ ፡ ፅድቅ ፡ ሲሆን ፡ ፅድቄ
ነፍሴን ፡ ተቀበል ፡ አምላኬ