አንተ ፡ የታመንክ ፡ የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ ሆይ (Ante Yetamenk Yenefsie Medhanit Hoy)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ አንተ ፡ የታመንክ
የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ ሆይ!
አትመጣም ፡ ወይ? (፪x)

አምላኬ ፡ ፊትህን ፡ አትሰውርብኝ
ድምፄን ፡ ስማልኝ ፡ ቅረብ ፡ አጽናናኝ

አዝ፦ አንተ ፡ የታመንክ
የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ ሆይ!
አትመጣም ፡ ወይ? (፪x)

እንግዳ ፡ ብቻ ፡ በምድር ፡ ነኝና
ገና ፡ አላየሁም ፡ የአንተን ፡ ብፅዕና

አዝ፦ አንተ ፡ የታመንክ
የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ ሆይ!
አትመጣም ፡ ወይ? (፪x)

በዚህ ፡ በእንግድነት ፡ አገር ፡ ሳለሁ
ወደ ፡ ሰማይህ ፡ በናፍቆት ፡ አያለሁ

አዝ፦ አንተ ፡ የታመንክ
የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ ሆይ!
አትመጣም ፡ ወይ? (፪x)

እስክትመጣም ፡ በልቤ ፡ ውስጥ ፡ ንገሥ
ሐዘኔን ፡ አቅልለህ ፡ ደስታዬን ፡ ቀድስ

አዝ፦ አንተ ፡ የታመንክ
የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ ሆይ!
አትመጣም ፡ ወይ? (፪x)

አንተን ፡ ብቻ ፡ አቤቱ ፡ እንድፈራ
ልቤ ፡ በመንፈስህ ፡ ዘወትር ፡ ይመራ

አዝ፦ አንተ ፡ የታመንክ
የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ ሆይ!
አትመጣም ፡ ወይ? (፪x)

የምትሰጠኝ ፡ ዘውድ ፡ እንዳይቀርብኝ
አምላኬ ፡ ሃይማኖትን ፡ ጨምርልኝ

አዝ፦ አንተ ፡ የታመንክ
የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ ሆይ!
አትመጣም ፡ ወይ? (፪x)