አንድ ፡ ነገር ፡ እናፍቃለሁ (And Neger Enafqalehu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ ፣
አንድ ፡ ነገር ፡ እናፍቃለሁ
ይህንንም ፡ እጓጓለሁ
ዕድሜ ፡ ልኬን ፡ በቤትህ ፡ እኖር ፡ ዘንድ (፬X)

ባገኝ ፡ ባጣ ፡ ልጐዳ
መኖር ፡ እመርጣለሁ ፡ በአንተ ፡ ጓዳ
ደጃፍህ ፡ ተጥሎ ፡ ክብርን ፡ ሁሉ ፡ አጥቶ
መኖር ፡ ይሻለኛል ፡ በቤትህ ፡ ተጠልቶ

አዝ ፣
አንድ ፡ ነገር ፡ እናፍቃለሁ
ይህንንም ፡ እጓጓለሁ
ዕድሜ ፡ ልኬን ፡ በቤትህ ፡ እኖር ፡ ዘንድ (፬X)

በዓለም ፡ ሆኜ ፡ ብገኝ ፡ ገናና
ኑሮዬ ፡ ቢደላኝ ፡ ባገኝ ፡ ዝና
አንተ ፡ ካልኖርክበት ፡ በዕለት ፡ ኑሮዬ
ሁሌ ፡ ወደ ፡ ጥፋት ፡ ይሆናል ፡ ሩጫዬ

አዝ ፣
አንድ ፡ ነገር ፡ እናፍቃለሁ
ይህንንም ፡ እጓጓለሁ
ዕድሜ ፡ ልኬን ፡ በቤትህ ፡ እኖር ፡ ዘንድ (፬X)

ፍቅርህ ፡ ማርኮኝ ፡ መጥቻለሁ
ከእንግዲህስ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ?
በዓመታት ፡ መካከል ፡ ድንቅን ፡ አይቻለሁ
ፀጋህ ፡ ስለበዛ ፡ ዛሬንም ፡ ቆሜያለሁ

አዝ ፣
አንድ ፡ ነገር ፡ እናፍቃለሁ
ይህንንም ፡ እጓጓለሁ
ዕድሜ ፡ ልኬን ፡ በቤትህ ፡ እኖር ፡ ዘንድ (፬X)

ዝዬ ፡ ልወድቅ ፡ ስንገዳገድ
አንተው ፡ አሳየኸኝ ፡ የድል ፡ መንገድ
ጠላቴን ፡ በድፍረት ፡ እንዳየው ፡ ረዳኸኝ
በሕያዋን ፡ መንገድ ፡ በብርሃን ፡ መራኸኝ

አዝ ፣
አንድ ፡ ነገር ፡ እናፍቃለሁ
ይህንንም ፡ እጓጓለሁ
ዕድሜ ፡ ልኬን ፡ በቤትህ ፡ እኖር ፡ ዘንድ (፬X)