አምላኬ ፡ ያደረገውን ፡ ነገር ፡ ሁሉ (Amlakie Yaderegewn Neger Hulu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ ፣
አምላኬ ፣
ያደረገውን ፡ ነገር ፡ ሁሉ
ባወራው (፬X)
ከቁጥር ፡ ሁሉ ፡ በዛ
ተዓምራቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ባወራው (፪X)

ኃጢአተኛን ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ አይቼ
እንደ ፡ ሊባኖስ ፡ ዛፍ ፡ ለምልሞ ፡ ፈርቼ
ተመልሼ ፡ ከቦታው ፡ ፈለግሁት
እንኳን ፡ እርሱን ፣ ሥፍራውን ፡ አጣሁት ።

አዝ ፣
አምላኬ ፣
ያደረገውን ፡ ነገር ፡ ሁሉ
ባወራው (፬X)
ከቁጥር ፡ ሁሉ ፡ በዛ
ተዓምራቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ባወራው (፪X)

የክፉ ፡ ኃይል ፡ በቁጣ ፡ ዓይኖቹ ፡ እያየኝ
ጥርሱን ፡ በላዬ ፡ ላይ ፡ ሲያንገጫግጭብኝ
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ አይቶ ፡ ስቆበታል
የመጥፊያው ፡ ቀን ፡ እንደደረሰ ፡ አውቋል

አዝ ፣
አምላኬ ፣
ያደረገውን ፡ ነገር ፡ ሁሉ
ባወራው (፬X)
ከቁጥር ፡ ሁሉ ፡ በዛ
ተዓምራቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ባወራው (፪X)

ከመቅደሱ ፡ ከሰማይ ፡ ከፍታ ፡ ላይ ፡ ሆኗል
ወደ ፡ ምድር ፡ በታች ፡ አሽቆልቁሎ ፡ አይቷል
የእሥረኞችን ፡ የጩኸት ፡ ቃል ፡ ሰምቷል
ከሞት ፡ አፋፍ ፡ ከፍርድ ፡ ወጥመድ ፡ ፈቷል

አዝ ፣
አምላኬ ፣
ያደረገውን ፡ ነገር ፡ ሁሉ
ባወራው (፬X)
ከቁጥር ፡ ሁሉ ፡ በዛ
ተዓምራቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ባወራው (፪X)

ከሰይጣን ፡ ኃይል ፡ የዳናችሁ ፡ ሁሉ ፡ ከሰይፉ
ለሚመጣው ፡ ትውልድ ፡ ጻፉና ፡ አስተላልፉ
አምላካችን ፡ ይህን ፡ ተዓምር ፡ ሠርቷል
እኔም ፡ ባወራው ፡ ባወራው ፡ ከቁጥር ፡ በዝቷል

አዝ ፣
አምላኬ ፣
ያደረገውን ፡ ነገር ፡ ሁሉ
ባወራው (፬X)
ከቁጥር ፡ ሁሉ ፡ በዛ
ተዓምራቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ባወራው (፪X)