አምላክ ፡ የፈለገው ፡ ከአንተ (Amlak Yefelegew Kante)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አምላክ ፡ የፈለገው ፡ ከአንተ
በግልጥ ፡ ተነግሯል
ሲገስጽ ፣ ሲመክር ፡ ለአንተ
ጥቅም ፡ ይሆንሃል

በገርነት ፡ በትሕትና
በአምላክ ፡ ቃል ፡ እመን
ተግተህ ፡ በቀና ፡ ሕሊና
ፈቃዱንም ፡ ፈጽም

በክርስቶስ ፡ ሁሉ ፡ ይቀናል
በኃይሉ ፡ ነህ ፡ ሥልጡን
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ይረዳሃል
ያሳይሃል ፡ ፍቅሩን

በቃሉ ፡ የሚያምኑ
ለጽድቅ ፡ አላቸው ፡ ኃይል
በምድር ፣ በሰማይ ፣ በእርሱ
ሰላም ፡ ብጹዕ ፡ ዕድል

በአንተ ፡ ነው ፡ የዓብ ፡ ሥምረት
የዓለም ፡ ተስፋ ፡ ነህ
ትላንት ፣ ዛሬ ፡ ሳትለወጥ
ገና ፡ ትኖራለህ !