Caleb Tesfaye/Tensae Ale/Sew Liela Liela Sil

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ካሌብ ተስፋዬ ርዕስ ሰው ሌላ ሌላ ሲል አልበም ትንሳኤ አለ

አለልኝ የምልብህ ትምክህቴ የምመካብህ የድሃ ቀኜ ምርኩዝ ነህ አለኝታ ነህ ታኮራለህ ማንም ባይኖረኝ ዙሪያዬ ማዶ ቢሆንም ጓዳዬ አለሁልህ የሚል ቢጠፋ ጌታ እኮ ነህ የእኔ ተስፋ

ሰው ሌላ ሌላ ሲል ሲኮራ በእንጀራው እኔ ግን ከእጅህ ነው ጠግቤ የምበላው (፪x) (ክላሲካል)

ከእሳት ይልቅ የበረታ ሰልፌ ኑሮ ጥዋት ማታ ደምህ ከለላ ሆኖኝ እንዳይፈጀኝ ጠብቆኝ ተጠነከክልኝና ባሕሩን ከፈልከውና ተሻገርኩኝ ሄድኩኝ ማዶ ነበር ነገር ሁሉ ከብዶ

መች ቀላል ሆነና ያለፍኩት ጐዳና ለመኖር በቃሁኝ በእጅህ ተያዝኩና (፪x) (ክላሲካ)

ሳየው ዞሬ ወደ ኋላ ባይኖረኝ የአንተ ከለላ ተረት ሆኜ ቀር ነበረ ምሕረትህ በዛ ጨመረ ከፈተና መውጫ ብሩ መኖር አንተን እየጠሩ አታሳፍር መልስ አለህ ለጭንቅ ቀን ደራስህ ነህ

ከጉድጓድ ከወጡ ከሞት ካመለጡ ከዚህ በላይ ደስታ ምን አለና ጌታ (፪x) (ክላሲካል)

ከእናት በላይ እናት ብልህ ከአባት በላይ አባት ብልህ አይበቃ ሥም ቢሰጥህ ከዚህ ሁሉ የላክ ነህ ሳልወድህ ስለ ወደድከኝ ሳልመርጥህ ስለ መረጥከኝ ንጉሥ ሆይ እኔም ምሥጋና አለኝ ከነኃጢአቴ ተቀበልከኝ

ጉድለቴን የሞላ አንተን የለ ሌላ ሞገስ ማዕረጌ ነህ ወግ ያየሁብህ (፪x)