፪ኛ ፡ ወደ ፡ ተሰሎንቄ ፡ ሰዎች - ምዕራፍ ፫ (2nd Thesallonians - Chapter 3)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


፩፡ በቀረውስ ፥ ወንድሞች ፡ ሆይ ፥ የጌታ ፡ ቃል ፡ እንዲሮጥ ፡ በእናንተም ፡ ዘንድ ፡ ደግሞ ፡ እንደሚሆን ፡ እንዲከበር ፥ እምነትም ፡ ለሁሉ ፡ ስለማይሆን ፡ ከዓመፀኞችና ፡ ከክፉዎች ፡ ሰዎች ፡ እንድንድን ፡ ስለ ፡ እኛ ፡ ጸልዩ። ፪፡ ነገር ፡ ግን ፡ የሚያጸናችሁ ፡ ከክፉውም ፡ የሚጠብቃችሁ ፡ ጌታ ፡ የታመነ ፡ ነው። ፫፡ የምናዛችሁንም ፡ አሁን ፡ እንድታደርጉ ፡ ወደ ፡ ፊትም ፡ ደግሞ ፡ እንድታደርጉ ፡ ስለ ፡ እናንተ ፡ በጌታ ፡ ታምነናል። ፬፡ ጌታም ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ወደ ፡ ክርስቶስም ፡ ትዕግሥት ፡ ልባችንን ፡ ያቅናው። ፭፡ ወንድሞች ፡ ሆይ ፥ ከእኛ ፡ እንደ ፡ ተቀበለው ፡ ወግ ፡ ሳይሆን ፡ ያለ ፡ ሥርዓት ፡ ከሚሄድ ፡ ወንድም ፡ ሁሉ ፡ ትለዩ ፡ ዘንድ ፡ በጌታችን ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ስም ፡ እናዛችኋለን። ፮፡ እኛን ፡ ልትመስሉ ፡ እንዴት ፡ እንደሚገባችሁ ፡ ራሳችሁ ፡ ታውቃላችሁና ፤ በእናንተ ፡ ዘንድ ፡ ያለ ፡ ሥርዓት ፡ አልሄድንምና ፤ ፯፡ ከእናንተ ፡ ዘንድ ፡ በአንዱ ፡ ስንኳ ፡ እንዳንከብድበት ፥ ሌሊትና ፡ ቀን ፡ በድካምና ፡ በጥረት ፡ እየሠራን ፡ እንኖር ፡ ነበር ፡ እንጂ ፥ ከማንም ፡ እንጀራን ፡ እንዲያው ፡ አልበላንም። ፰፡ ይህም ፡ እኛን ፡ ልትመስሉ ፡ ራሳችንን ፡ እንደ ፡ ምሳሌ ፡ እንሰጣችሁ ፡ ዘንድ ፡ ነበር ፡ እንጂ ፥ ያለ ፡ ሥልጣን ፡ ስለ ፡ ሆንን ፡ አይደለም። ፱፡ ደግሞ ፡ ከእናንተ ፡ ጋር ፡ ሳለን። ሊሠራ ፡ የማይወድ ፡ አይብላ ፡ ብለን ፡ አዘናችሁ ፡ ነበርና። ፲፡ ሥራ ፡ ከቶ ፡ ሳይሠሩ ፥ በሰው ፡ ነገር ፡ እየገቡ ፥ ያለ ፡ ሥርዓት ፡ ከእናንተ ፡ ዘንድ ፡ ስለሚሄዱ ፡ ስለ ፡ አንዳንዶች ፡ ሰምተናልና። ፲፩፡ እንደነዚህ ፡ ያሉትንም ፡ በጸጥታ ፡ እየሠሩ ፡ የገዛ ፡ እንጀራቸውን ፡ ይበሉ ፡ ዘንድ ፡ በጌታችን ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ እናዛቸዋለን ፡ እንመክራቸውማለን። ፲፪፡ እናንተ ፡ ግን ፥ ወንድሞች ፡ ሆይ ፥ መልካም ፡ ሥራን ፡ ለመሥራት ፡ አትታክቱ። ፲፫፡ በዚህ ፡ መልእክት ፡ ለተላከ ፡ ቃላችን ፡ የማይታዘዝ ፡ ማንም ፡ ቢኖር ፥ ይህን ፡ ተመልከቱት ፥ ያፍርም ፡ ዘንድ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ አትተባበሩ። ፲፬፡ ነገር ፡ ግን ፡ እንደ ፡ ወንድም ፡ ገሥጹት ፡ እንጂ ፡ እንደ ፡ ጠላት ፡ አትቍጠሩት። ፲፭፡ የሰላምም ፡ ጌታ ፡ ራሱ ፡ በሁሉ ፡ መንገድ ፡ ዘወትር ፡ ሰላምን ፡ ይስጣችሁ። ጌታ ፡ ከሁላችሁ ፡ ጋር ፡ ይሁን። ፲፮፡ በገዛ ፡ እጄ ፡ የተጻፈ ፡ የእኔ ፡ የጳውሎስ ፡ ሰላምታ ፡ ይህ ፡ ነው ፤ የመልእክቴ ፡ ሁሉ ፡ ማስረጃ ፡ ይህ ፡ ነው ፤ እንዲህ ፡ እጽፋለሁ። ፲፯፡ የጌታችን ፡ የኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ጸጋ ፡ ከሁላችሁ ፡ ጋር ፡ ይሁን።













Navigation menu

MediaWiki spam blocked by CleanTalk.