፩ኛ ፡ ወደ ፡ ተሰሎንቄ ፡ ሰዎች - ምዕራፍ ፫ (1st Thesallonians - Chapter 3)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


፩፡ ስለዚህ ፡ ወደ ፡ ፊት ፡ እንታገሥ ፡ ዘንድ ፡ ባልተቻለን ፡ ጊዜ ፥ በአቴና ፡ ብቻችንን ፡ ልንቀር ፡ በጎ ፡ ፈቃዳችን ፡ ሆነ። ፪፡ ስለ ፡ እምነታችሁም ፡ እንዲያጸናችሁና ፡ እንዲመክራችሁ ፡ ወንድማችንን ፡ የእግዚአብሔርንም ፡ አገልጋይ ፡ ከእኛ ፡ ጋርም ፡ አብሮ ፡ በክርስቶስ ፡ ወንጌል ፡ የሚሠራውን ፡ ጢሞቴዎስን ፡ ላክነው ፤ ፫፡ በዚህ ፡ መከራ ፡ ማንም ፡ እንዳይናውጥ ፥ ለዚህ ፡ እንደ ፡ ተመረጥን ፡ ራሳችሁ ፡ ታውቃላችሁና። ፬፡ በእውነት ፡ ከእናንተ ፡ ጋር ፡ ሳለን ፥ መከራ ፡ እንቀበል ፡ ዘንድ ፡ እንዳለን ፡ አስቀድመን ፡ እንነግራችሁ ፡ ነበር ፤ እንዲሁም ፡ ደግሞ ፡ ሆነ ፥ ይህንም ፡ ታውቃላችሁ። ፭፡ ስለዚህ ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ ወደ ፡ ፊት ፡ እታገሥ ፡ ዘንድ ፡ ባልተቻለኝ ፡ ጊዜ። ፈታኝ ፡ ምናልባት ፡ ፈትኖአቸዋል ፡ ድካማችንም ፡ ከንቱ ፡ ሆኖአል ፡ ብዬ ፡ እምነታችሁን ፡ ለማወቅ ፡ ላክሁ። ፮፡ አሁን ፡ ግን ፡ ጢሞቴዎስ ፡ ከእናንተ ፡ ዘንድ ፡ ወደ ፡ እኛ ፡ መጥቶ ፡ ስለ ፡ እምነታችሁና ፡ ስለ ፡ ፍቅራችሁ ፡ የምስራች ፡ ብሎ ፡ በነገረን ፡ ጊዜ ፥ እኛም ፡ እናያችሁ ፡ ዘንድ ፡ እንደምንናፍቅ ፡ ታዩን ፡ ዘንድ ፡ እየናፈቃችሁ ፡ ሁልጊዜ ፡ በመልካም ፡ እንደምታስቡን ፡ በነገረን ፡ ጊዜ ፥ ፯፡ ስለዚህ ፥ ወንድሞች ፡ ሆይ ፥ በእምነታችሁ ፡ በኩል ፡ በችግራችንና ፡ በመከራችን ፡ ሁሉ ፡ ስለ ፡ እናንተ ፡ ተጽናናን ፤ ፰፡ እናንተ ፡ በጌታ ፡ ጸንታችሁ ፡ ብትቆሙ ፥ አሁን ፡ በሕይወት ፡ እንኖራለንና። ፱፡ ፊታችሁን ፡ ልናይ ፡ በእምነታችሁም ፡ የጎደለውን ፡ ልንሞላበት ፡ ሌሊትና ፡ ቀን ፡ ከመጠን ፡ ይልቅ ፡ እየጸለይን ፡ በአምላካችን ፡ ፊት ፡ ከእናንተ ፡ የተነሣ ፡ ስለምንደሰተው ፡ ደስታ ፡ ሁሉ ፥ ለእግዚአብሔር ፡ በእናንተ ፡ ምክንያት ፡ ምን ፡ ያህል ፡ ምስጋና ፡ እናስረክብ ፡ ዘንድ ፡ እንችላለን ? ፲፡ አምላካችንና ፡ አባታችን ፡ ራሱ ፡ ጌታችንም ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ወደ ፡ እናንተ ፡ መንገዳችንን ፡ ያቅና ፤ ፲፩፡ ጌታችንም ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ከቅዱሳኑ ፡ ሁሉ ፡ ጋር ፡ ሲመጣ ፥ በአምላካችንና ፡ በአባታችን ፡ ፊት ፡ በቅድስና ፡ ነቀፋ ፡ የሌለበት ፡ አድርጎ ፡ ልባችሁን ፡ ያጸና ፡ ዘንድ ፥ እኛ ፡ ደግሞ ፡ ለእናንተ ፡ እንደምንሆን ፡ ጌታ ፡ እርስ ፡ በእርሳችሁ ፡ ያላችሁን ፡ ለሁሉም ፡ የሚሆን ፡ ፍቅራችሁን ፡ ያብዛ ፡ ይጨምርም።
















Navigation menu

MediaWiki spam blocked by CleanTalk.