የሕይወቴ ፡ መስራች (Yehiwote Mesrach) - ቤዛ ፡ ሳሙኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
ቤዛ ፡ ሳሙኤል
(Beza Samuel)

Lyrics.jpg


(1)

የሕይወቴ ፡ መስራች
(Yehiwote Mesrach)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤዛ ፡ ሳሙኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Beza Samuel)

ግማሹን ለጌታ ግማሹን ለእኔ አልልህ
ሕይወቴን በሙሉ ሰጠሁህ ሳላንገራግር
የሕይወቴ ጀማሪ ፈጻሚም አንተው ነህና
ሳልሰስት ሰጠሁህ ስራበት ዛሬም እንደገና
 
ሕይወቴ ያንተ ነውና
ዘመኔ ያንተ ነውና
ጉብዝናዬ ያንተ ነውና
ያንተ ነውና

በኖርኩባት በዚህች ጥቂቷ ዘመን
ብዙ አይቻለሁ ወጪ ወራጁን
አንዱም አያዛልቅ ውበት የለበት
ኢየሱስ አንተ ነህ የህይወቴ ድምቀት
የህይወቴ የህይወቴ ድምቀት (፫x)

ህይወቴ ያንተ ነውና
ዘመኔ ያንተ ነውና
ጉብዝናዬ ያንተ ነውና
ያንተ ነውና

እንግዲህ በቀረኝ በመጪው ዘመኔ
ልጅህን እንድመስል የኖረውን ኖሬ
ሸክላ ሰሪ ሸክላው በእጁ እንዳለ
ሰሪዬ ነህና የእኔም አንተ አለህ

እንደወደድከው እንደፈቀድከው አድርገው
ቀድሞም ያንተ ነው አሁንም ላንተው አድርገው
ጉብዝናም የምለው ጉልበት የምለው ካንተ ውጪ
አንተው ጋ ልኑር ነፍሴም እጅግ ወዳሃለች

እንድኖር ስታዝዘኝ በእናቴ ማህጸን
አስበኸኝ ኖሯል አባት እንድትሆነኝ
የህይወቴ መስራች ሰሪዬ ነህና
እንደፈለክ አርገው ጌታ ስራበታ
ጌታ ጌታ ስራበታ ጌታዬ ጌታ ስራበታ
ጌታ ጌታ ስራበታ

ግማሹን ለጌታ ግማሹን ለእኔ አልልህ
ህይወቴን በሙሉ ሰጠሁህ ሳላንገራግር
የህይወቴ ጀማሪ ፈጻሚም አንተው ነህና
ሳልሰስት ሰጠሁህ ስራበት ዛሬም እንደገና

ህይወቴ ያንተ ነውና
ዘመኔ ያንተ ነውና
ጉብዝናዬ ያንተ ነውና
ያንተ ነውና