ምህረቱን አስቤ (Mehretun Asibe) - ቤተልሔም ተዘራ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቤተልሔም ተዘራ
(Bethelehem Tezera)

Lyrics.jpg


(2)

ተፈፀመ
(Tefetseme)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethelehem Tezera)

ዝም ብዬ ሳስብ ሳሰላስለው
እግዚአብሔር እንዴት ድንቅ ነው (፫x)
ዝም ብዬ ሳስብ ሳሰላስለው
እግዚአብሔር እንዴት ድንቅ ነው (፫x)

አዝ፦ ምሕረቱን አስቤ አቤት ስል ፍቅሩ አለ ለካ አሃ
ፍቅሩን አስቤ አቤት ስል ባርኮቱ አለ ለካ አለ ለካ
ኧረ እንዴት አመስግኜው ልርካ (፬x)

አልጠፋብሽ ያለኝ ከልቤ ውስጥ የእግዚአብሔርስ ፍቅር
አሳዳጊነቱ አባትነቱ ከህይወቴ ጅምር
ትዝታ አይደለም እያነሳሁ ምተርክለት
በርሱ አይደለም ወይ እስከ አሁኗ ድረስ ያለሁት (፪x)

የእግዚአብሔር ምህረት አቤት አቤት አቤት
ሰው ወዳድነትህ አቤት አቤት አቤት
የፍቅሩ ጥልቀት አቤት አቤት አቤት
እሩህሩህነትህ አቤት አቤት አቤት (፪x)

አንድ ሁለት ብዬ ውለታውን አስቤ ልቆጥር
ጥፍት ይለኛል ከየት ተነስቼ እንደምጀምር
ይህ እንኳን ቢረዳኝ ቢነግርልኝ ውስጤን ቢገልጸው
እንደእግዚአብሔር ያለ የለም ብዬ ልደምድመው (፪x)

እንደእግዚአብሔር የለም አቤት አቤት አቤት
ቢፈለግ ዘላለም አቤት አቤት አቤት
እንደእሱ የለም አቤት አቤት አቤት
ቢፈለግ ዘላለም አቤት አቤት አቤት (፪x)

አዝ፦ ምሕረቱን አስቤ አቤት ስል ፍቅሩ አለ ለካ አሃ
ፍቅሩን አስቤ አቤት ስል ባርኮቱ አለ ለካ አለ ለካ
ኧረ እንዴት አመስግኜው ልርካ(፬x)